የሠራዊቱ ቀንና የሠራዊቱ ክብር
በሰሎሞን ተሰማ ጂ. semnaworeq.blogspot.com



አባ ባሕርይ እንዳተተው የክርስቲያኑ ጦር የተደራጀባቸው ዐስሩ ደንቦች የሚከተሉት ናቸው፡፡
አንደኛ፤ መነኮሳት ናቸው፡፡ እነዚህም ቁጥራቸው
ብዙ ነበር፡፡ ዋና ተግባራቸውም ጸሎት ማድረግ ስለሆነ ዘመቻ አይወጡም፡፡ ሁለተኛ፤ ደባትር ናቸው፡፡ እነዚህም ሥራቸው በማኅሌትና በዝማሬ እግዚአብሔርን ማመስገን ስለሆነ ዘመቻ
አይወጡም፡፡ ሦስተኛ፤ ዣን ሐፀናና ዣን ማሰሬዎች
ናቸው፡፡ እነዚህም ቢሆኑ ዋና ሥራቸው ወንበርተኞች/የወረዳ ወይም የቀበሌ ካድሬዎችና የቀላድ ጣዮች ስለሆኑ ዘመቻ አይወጡም፡፡ አራተኛ፤ የሴት ወይዛዝርት ደጋፊዎች ናቸው፡፡ እነዚህም
ቢሆኑ ወይዘሮዎችን ማጀብ ስለሆነ ሥራቸው ለዘመቻ አይወጡም ነበር፡፡ አምስተኛዎቹ
ደንበኞችም፤ ሽማግሎች ናቸው፡፡ እነዚህም “ወባዜ” ይባሉ ነበር፡፡ ዋና ሥራቸው ርስት ማካፈል ብቻ ስለነበረ፤ ወደዘመቻ አይወጡም
ነበር፡፡ ስድስተኛ፣ አራሾች ናቸው፡፡ እነዚህም
ቢሆኑ ከእርሻ በስተቀር ሌላ ሥራ አያውቁም ነበር፡፡ ሰባተኛ፤
ነጋዴዎች ናቸው፡፡ እነዚህም ቢሆኑ መሸጥና መለወጥ እንጂ ውጊያን ስለማያውቁ ዘመቻ አይወጡም ነበር፡፡ ስምንተኛ፤ የእጅ ባለሙያዎች ናቸው፡፡ እነዚህም ቢሆኑ
በሽመና፣ በቀጥቃጭነትና በአንጥረኝነት እንዲሁም በልዩ ልዩ ሥራዎች ይሰማራሉ እንጂ ወደዘመቻ አይሄዱም ነበር፡፡ ዘጠነኛው ረድፍ ላይ ያሉት ደንበኞች ደግሞ፤ የኪነት
ሰዎች ናቸው፡፡ እነዚህም ቢሆኑ በአዝማሪነትና በአመሸታ ቤት ይሆናሉ እንጂ ወደዘመቻ ለውጊያ አይሄዱም ነበር፡፡ ዐሥረኞቹና የመጨረሻዎቹ፣ ጋሻ ጃግሬ የሚባሉት ናቸው፡፡
እነዚህ ወታደሮች ናቸው፡፡ ዋና ሥራቸውም ውጊያ ነበር፡፡ ይህም የመጨረሻው ደንብ ቁጥሩ አነስተኛ ስለነበረ፤ “ጠፍአት ሀገርነ (አገራችን
ጠፋች)” በማለት አባ ባሕርይ ይደመድማል፡፡



በሁለተኛ ደረጃም የሚነሳው ነጥብ፣ ስለሠራዊቱ “ሁሉንም ልቆጣጠር፣ ሁሉንም ልሽጥ-ልሸቅጥ” የሚለው አባዜ
ነው፡፡ ይህም ከላይ ከጠቀስነው ከፍተኛውን ወታደራዊ ሥልጣን ከያዙት የአንድ ፓርቲ/ራስና ደጃዝማቾች የግል ጥቅምና ፍላጎት ጋር
የተሣሰረ አደጋ ነው፡፡ በቀጥታ ከገንዘብና ከጥቅም ጋር የተቆራኘ ነው፡፡ ብዙዎቹ ግዙፍ የመዋለ-ንዋይና የቴክኖሎጂ አቅምን ይዘው
የተደራጁ ናቸው፡፡ ለምሳሌ የመከላከያ ብረታ-ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽንን፣ የላሊበላ ኮንስትራክሽንን መውሰድ እንችላለን፡፡
በቢሊዮኖች የሚቆጠር የምዕዋለ-ንዋይ አላቸው፡፡ ሆኖም ግን ከፍተኛ አመራራቸው ከቅድመ 1983 ዓ.ም በፊት ከነበረው መንፈስ ብዙም
የራቀ አይደለም፡፡ የአንድ ቡድን የበላይነት ጎልቶ ይታይበታል፡፡ ከጥበቃ እስከ ባለሙያና የመምሪያ ኃላፊዎች ድረስ የአንድ ቡድን/ፓርቲ
የጎላ ቁጥጥርና ርብርብ ይንፀባረቅበታል፡፡ ለምን ኢትዮጵያዊ እንዲሆን አይደረግም? ለምንስ የአንድ ቡድን/ፓርቲ ቀልብና መንፈሥ
ብቻ እንዲንጸባረቅበት ተፈለገ? ለመሆኑ የእስራኤልን ወይም የግብጽን መከላከያ ሞዴል አድርጎ መነሳቱ ባልከፋ፡፡ ነገር ግን፣ ለምን
እንደስራኤልና እንደግብጽ ሀገራዊ ቅርጽና መልክ እንዲኖረውስ አልተደረገም? መልሱ ቀላል ነው፡፡ የራሶችና የደጃዝማቾች መንፈስ ዛሬም
ስላለ ነው፡፡ ሁሉም በየፊናው “ዘመናዊ ፊታውራሪ” ለመሆን ቋምጧል፡፡

ሌላም ተያያዥ ችግር አለ፡፡ ይኼውም በሠራዊቱ ውስጥ ካሉት የተማሩ ሙያተኞች ጥቅምና መብት
ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ይህንን ሃሳብ በምሳሌ ማስረዳቱ ያዋጣል፡፡ አንድ የማስተርስ ዲግሪ ያለው የትኛውም የመከላከያ ከፍተኛ የትምህርት
ተቋማት ውስጥ ያለ ባለሙያ የሚከፈለው ደሞዝ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የደሞዝ ስኬል መሠረት ነው፡፡ የቤት አበልም አለው፡፡ በአጠቃላይ
አንድ የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ያለ የሲቪል ባለሙያ የሚከፈለው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ያለ ማንኛውም የማስተርስ ዲግሪ
ምሩቅ የሚከፈለውን ደሞዝ ነው፡፡ ነገር ግን፣ አንድ የመከላከያ የኒቨርሲቲ ውስጥ የሚሠራ መሳሳይ የት/ት ደረጃ ያለው ባለሙያ ከዚህ
በጣም ያነሰ ክፍያ ነው ያለው፡፡ ለምን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አዋጅ
በወሰነው መሠረት እንደማይከፈላቸው የተብራራ ነገር የለም፡፡ ዋናው ምክንያት ግን፣ “የከፍተኛ መኮንኖች ደሞዝ ስንት
ነው?” የሚለው ነው፡፡ እጅግ በጣም አስገራሚ ነው፡፡ በተለይም በፋይናንሻል ተቋማት (በባንኮች፣ በኢንሹራንስ ተቋማት)፣ በግንባታ
ድርጅቶችና በመንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ያሉ ኃላፊዎች ከሚከፈላቸው ጋር ካነጻጸርነው እጅግ አናሳ ነው፡፡
ይህንንም ጉዳይ በምሳሌ ብናወሳው ሳይሻል አይርም፡፡ አንድ የግል ባንክ ውስጥ የሚሠራና
በሥሩ አራት መቶ ሃምሳ የማይሆኑ ሰራተኞችን የሚመራ የባንክ ሥራ-አስፈጻሚ ከሠላሳ ሺህ ብር በላይ ይከፈለዋል፡፡ በዚያ ላይ ቢያንስ
ሁለት መኪናዎችና የቤት አበል፣ እንዲሁም የተለያዩ ጥቅማ-ጥቅሞች አሉት፡፡ ይህ ሰው ልጆቹን የተሻለ ትምህርት ቤት ልኮ ያስተምራል፡፡
ዘመዶቹ ሲመጡ የቻለውን ያህል የሚረዳበት ገንዘብም አለው፡፡ መስረቅም ሆነ ሙስና ውስጥ መግባቱ (ዓመል ካልሆነበት በስተቀር) እምብዛም
አያስፈልገውም፡፡ አንድ የዓለም አቀፍ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ውስጥ የሚሠራም የብሔራዊ ድርጅት ሥራ-አስኪያጅ ከሠላሳ ሺህ ብር
በላይ የከፈለዋል፡፡ እንደባንኩ ሥራ-አስፈጻሚ ሁሉ፣ የመኪና፣ የቤትና የተለያዩ ጥቅማ-ጥቅሞች አሉት፡፡ ልጆቹን የተሻለ ትምህርት
ቤት ማስተማርም ሆነ ለወደፊቱ መጦሪያውን ማስቀመጥ/መቆጠብ ይችላል፡፡ ነገር ግን፣ የአንድ የዕዝ ኃላፊ የሆነ ጄኔራል ክፍያ በጣም
ዝቅተኛ ነው፡፡ እርግጥ ነው የቤት፣ የመኪናና የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች ቢኖሩትም ቅሉ፤ ደሞዙ የባንኩን ወይም የመንግሥታዊ የልሆነ
ድርጅት ውስጥ የሚሠራውን ሰው ደሞዝ አንድ ስድስተኛ (1/6) ገደማ ቢሆን ነው፡፡
ይህ ደሞዝና የገቢ ምንጭ አንድን የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራር የሚያተጋው አይደለም፡፡
ምናልባትም ለመርኅ መከበርም በጽናት እንዲቆም ላያደርገው ይችል ይሆናል፡፡ ስለሆነም፣ ስልጣኑም ሆነ ከስልጣኑ የሚገኘው ጥቅም
“የዛፍ ላይ ዕንቅልፍ” ከመተኛት ብዙም የተለየ አይሆንም፡፡ ደንበኛ እንቅልፍ ለመተኛት ደግሞ የአንዱ ቡድን/ፓርቲ አባል መሆን
የግድ ይላል፡፡ አለበለዚያ፣ በፖለቲካ ታማኝነት የሚሰጠው ከብ/ጄነራል በላይ ያሉትን ማዕረጎች ማሰብ ቀርቶ ማለምም አይቻልም፡፡
በዚህ መስመርና በዚህ ታማኝነት የሚመጡ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ደግሞ እንደምን አድርገው የመከላከያው ውስጥ ያሉትን የሠራዊቱ
አባላትና ሙያተኞች መብትና ጥቅም ሊያስከብሩ እንደሚችሉ መሰቡ ራሱ ከባድ ችግር አለው፡፡ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖቹ ተጠሪነታቸው
ለሾማቸው አካል እንጂ ለሚመሩት ሠራዊትና ሙያተኞች አለመሆኑ ስለሚያመዝን ነው፡፡ ስለሆነም፣ አንድ የማስተርስ ዲግሪ ያለው መቶ
አለቃ የሚከፈለው ክፍያ፤ ከሲቪሉ ጋር ተመሳሳይ ሥራ እያከናወነ ከሙያውና ከትምህርቱ ጋር የማይመጣጠን ነው፡፡ “ለምን ሆነ?” የሚል
ካለ መልሱ ቀላል ነው፡፡ የመከላከያ የደሞዝ እርክን ማሻሻያ የሚያስፈልገው ስለሆነ ነው፡፡ (መዘንጋት አልነበረበትም፤ ግን ተዘንግቷል፡፡)

የመከላከያ ሠራዊቱ ከክልላዊነት ስሜቱ ወጥቶ የብሔራዊነት ስሜትንም እንዲላበስ ሊከበሩለት
የሚገቡ የክብር፣ የመብትና የጥቅም ጉዳዮች ቅድሚያ ተሰጥቷቸው መከናወን አለባቸው፡፡ አሁኑኑ፣ በአፋጣኝ የመከላከያ ሠራዊቱን ከፍተኛ
አመራር በኢትዮጵያዊነት መርኆና የብሔራዊ ስሜት አብነትን ባረጋገጡ ኃላፊዎች መተካት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው፡፡ የጋራ ቤታችንን
ኢትዮጵያን የሚጠብቀውና ለነፃነቷ የሚጋደለው ከተለያዩ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ሆኖ ሳለ፣ እነዚህን ሙሉ-ለሙሉ የማይወክል
አመራር ቆም ብሎ ማሰብ ይጠበቅበታል፡፡ ሰባ በመቶ (70%) የሚሆነው የመላከያ ሠራዊት እስከ አፍንጫው ታጥቆ፣ አንድ ክልል ላይ
ብቻ ለምን እንደተከማቸም ሊመረመር ይገባዋል፡፡ መከላከያው ራሱን እንዲመረምር ጊዜውም ዕድሉም አለውና ፋታ ወስዶ ይመርምር፡፡

ከዚህ በተረፈ፣ እንኳንም የመከላከያ ሠራዊቱን ቀን ለማክበር ጅማሮው መታየቱ መልካም ነው፡፡
ሆኖም፣ በአምስቱም ዕዞችና በየክፍለ ጦሮቹ ብቻ በሚደረግ የወታደራዊ ትርኢትና ኤግዚቢሽን ብቻ ከሚወሰን በተለያዩ ክፍለ ጦሮችና
ዕዞች አማካይነት በሚደረጉ ስፖርታዊ ውድድሮችም ታጅቦ ቢቀርብ መልካም ነው እንላለን፡፡ በርካታ ቁጥር ያላቸውን የመከላከያ ሠራዊቱ
አባላትንም ሆነ የሕዝቡን ተሳትፎ ለማግኘት ያስችላል፡፡ በ1950 ዓ.ም ጀምሮ ይደረግ የነበረውና ቀዳሚው “የመከላከያ ሰራዊት ቀን”
እንዴት ይደረግ እንደነበርም ታሪክን መርምሮ መነሳቱ ያዋጣል፡፡ እነዚህን “የመከላከያ ሠራዊት ቀን” አከባበሮች በተመለከተ የምድር
ጦር፣ የአየር ኃይልም ሆነ የክብር ዘበኛ ተቋማት እያንዳንዳቸው ከዐሥር በላይ የክብረ በዓሉን አስመልከቶ ዘጋቢ መጽሔቶችን አሳትመው
ነበር፡፡ ስለሆነም፣ ታሪክን አጥንቶና መርምሮ ከታሪክ መማርና የተሻለ ለመሥራት መሞከርም ይገባል፡፡ (በቸር ያቆየን!)
"የአህመድ ግራኝን ወረራ ማን መከተው" kakaka…how can you say a civil war between Ethiopians is an invasion? This is simply a dragon leftist or "Atse" ideology. Whether you like it or not He is Ethiopian and rule Ethiopia for 13 years until the Portuguese mercenaries and the North "banda" takeover his power. This was the situation in the past Ethiopian, where rulers fought each other to control the power, in pretext of religion.
ምላሽ ይስጡሰርዝThank you, sir for your insightful replay. Please, keep it up.
ሰርዝThe Editor of semnaworeq.
I've gone through the text, u have managed to vividly expose the shameful race for grabbing the entire resource of the country thereby paving the way towards its ultimate disintegration which will be witnessed soon......Inexplicably awesome talent of looking at things from unbiased and absolutely impartial perspective. Sol do I've any choice other than being ur ardent fan and reader?! God bless u!
ምላሽ ይስጡሰርዝ