የመለስ፣ የጳውሎስና የቀ.ኃ.ሥ ፋውንዴሽኖች
በሰሎሞን ተሰማ ጂ. semnaworeq.blogspot.com

አዲስ ዘመን በገጽ አንድና ሁለት ላይ
እንዳሠፈረው፤ “መለስ ፋውንዴሽን ሊቋቋም ነው” ካለ በኋላ፣ “የህዝብ
ተወካዮች
ምክር ቤት የመለስ ፋውንዴሽን ማቋቋሚያ አዋጅን መርምሮ አጸደቀ፤” ሲልም ያክላል፡፡ ምክር
ቤቱም ሆነ አዲስ ዘመን “ፋውንዴሽን” ያሉት የአማርኛውን “በጎ አድራጎት ድርጅት” ለማለት ነው፡፡ ሌላ
ትርጉም የለውም፡፡ (“በጎ” ስላሰቡም ሊበረታቱ ይገባል፡፡ ግና፣ “መሸፋፈኑና ማለባበሱ ለምን አስፈለገ?” የሚለውን ጥያቄ አሁንም ልንደግመው እንወዳለን፡፡) አዲስ ዘመን እንዳለው፤ “አዋጁ የጸደቀው ክቡር አቶ መለስ ዜናዊ በህይወት ዘመናቸው ሲታገሉለት የነበሩትን የልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስት፣ የሰዎች ዴሞክራሲያዊ ግንኙነት፣ እኩልነት ክብርና ብልጽግና እንዲረጋገጥ ብሎም የሰላም ጅምሮቻቸውን ማስቀጠል እንዲቻል ነው፡፡
4ኛው ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛአመት የስራ ዘመን 13ኛ
መደበኛ ስብሰባውን ጥር 9/2005 ባካሄደበት
ወቅት ነው አዋጁን ያጸደቀው፡፡
“የፋውንዴሽኑ መቋቋም አቶ መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በእኩልነት፣ በመከባበርና በአንድነት የሚኖሩባት አገር እንድትሆን ከልጅነት እስከ እልፈተ ህይወታው የከፈሉትን መስዋዕትነት ለመዘከር ያስችላል ብለዋል፡፡
በአገራችን ሰላም፣ መልካም አስተዳደርና ዴሞክራሲ እንዲሰፍን ለማድረግ የሰጡትን አመራር ለማስታወስና በአፍሪካ አስተማማኝ ሰላም እንዲረጋገጥ ከፍተኛ አርአያት ያለው ተግባር የፈጸሙ በመሆናቸው ፋውንዴሽኑ እንዲቋቋም አስፈልጓል ነው” ያሉት አቶ አስመላሽ ፡፡
የምክር ቤቱ
የህግ፣ ፍትህና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ እንዲህ
አሉ፤ “የልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስት አስተሳሰብን ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ፋውንዴሽኑ ያለውን አስተዋፆዖ”
በተመለከተም ሲያብራሩ፤ “ፋውንዴሽኑ
የክቡር አቶ መለስ ዜናዊ አስክሬን የሚያርፍበትና በህዝብ የሚጎበኝበትን መናፈሻ መገንባትና ማስተዳደር እንደዚሁም አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ቤተመጻህፍት በመገንባት እርሳቸው የጻፏቸውን የተለያዩ መጽሐፍትና የተሰሩ ጥናታዊ ፊልሞች እንዲገኙበት ያደርጋል።
“በህዝቦችና በአገራት መካከል የመግባባትና የመተባበር መንፈስ እንዲዳብር በተለያዩ መንገዶች ትምህርት መስጠትና በኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ ዴሞክራሲያዊ እና በሰላም አስተሳሰብ ምርምር ለሚያደርጉ ሁሉ አስፈላጊ ሁኔታዎችን ማመቻቸትም ሌላው የፋውንዴሽኑ ተግባር እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
በችግር ምክንያት ትምህርታቸውን መከታተል ለማይችሉ ዜጎች በተለይም ለሴቶች የነጻ የትምህርት እድል ለመስጠትና የአረንጓዴ ልማት አስተሳሰብ ማስፋፋት፣ መተግበርና መደገፍ የፋውንዴሽኑ ዋና ዋና ተግባራት” እንደሆኑም
የጋዜጣው ዘገባ ያትታል፡፡
ወገንተኛው “ሪፖርተር”
ጋዜጣም በበኩሉ፣ “የመለስ ፋውንዴሽን አዋጅ ፀደቀ!” ሲል ጮቤ ረግጦ
ከጣራ በላይ በደስታ ጮኋል፡፡ ይህንንም የሚያሳብቁት እነዚህ ዐረፍተ ነገሮች ናቸው፡፡ “በሕይወት ዘመናቸው ያለ ዕረፍት ለኢትዮጵያ
ሕዝቦች
ካበረከቱት
በተጨማሪ
ለአፍሪካውያን
ሰላምና
ደኅንነት፣
በዓለም
መድረክ
የአፍሪካን
ጥቅም
ለማስከበር
ያደረጉትን
አስተዋጽኦ፣
እንዲሁም
በዓለም
የአየር
ንብረት
ላይ
የተጫወቱትን
የአረንጓዴ
አብዮት
ሚና
መዘከር
ከትውልድ
ወደ
ትውልድ
እንዲሸጋገር
ማድረግ፣
የመለስ
ፋውንዴሽን
መሠረታዊ
ዓላማዎች
መሆናቸውን
አዋጁ
እንደሚያስረዳ” ሪፖርተር ገልጧል፡፡ (ልብ በሉ፣ ይህንን ሁሉ ሃተቤተሰቦቻቸው፣
መንግሥት፣
ባለሀብቶችና
ጓደኞቻቸው
ፋውንዴሽኑን
ለማቋቋም
በሚያዋጡት
ገንዘብ
ድርሻ
እንደሚኖራቸው
ታና ውዳሴ የተናገረው
ሪፖርተር ጋዜጣ እንጂ አዲስ ዘመን አይደለም፡፡) ሪፖርተር አክሎም፤ “በቅርቡ ከፓርላማው
አባላት
የቀረቡ
ጥያቄዎችን
ለመመለስ
ተገኝተው
የነበሩት
ጠቅላይ
ሚኒስትር
ኃይለ
ማርያም
ደሳለኝ
በዚሁ
የመለስ
ፋውንዴሽን
ዙሪያ
ገለጻ
ማድረጋቸው
ይታወሳል፡፡
ገልጸዋል፡፡
ውይይቱን
ጋዜጠኞች
እንዳይከታተሉት
ዝግ
በመደረጉ
ግን
ዝርዝር
የፋውንዴሽኑ
ባለድርሻዎችንና
ሌሎች
ተያያዥ
ጉዳዮችን
ለማቅረብ
አልተቻለም፤”
ሲል ያቅማማል፡፡
“የመለስ ፋውንዴሽን/በጎ
አድራጎት ድርጅትንም” በተመለከተ ከሚነሱት ጥያቄዎች መካከል አንዱ ይሄው የማቋቋሚያ ገንዘብ ወጪ ነው፡፡ አቶ ኃይለ ማርያም
ደሳለኝ እንዳሉት፣ “ቤተሰቦቻቸው፣ መንግሥት፣
ባለሀብቶችና
ጓደኞቻቸው
ፋውንዴሽኑን
ለማቋቋም
በሚያዋጡት
ገንዘብ
ድርሻ
እንደሚኖራቸው” ተወስቷል፡፡
“የማን ድርሻ ምን ያህል ይሆናል?” እና “በምን ያህል ጊዜስ ውስጥ መዋጮው ተግባራዊ ይሆናል?” የሚሉትን ባለማብራራቱ
ጥርጣሬውን ከፍ ያደርገዋል፡፡ በተለይም፣ “ባለሀብቶች” የሚያዋጡት ገንዘብ መጠን በመቶኛ ካልተገደበ በስተቀር፣ ለሙስናና
ለእከክልኝ-ልከክልህ በር ይከፍታል፡፡ በውጭው ዓለም የበጎ አድራጎት መዋጮዎች ሲደረጉ፣ ድርጅቶቹ ለሚከፍሉት/ለሚለግሡት
የኮርፖሬት መዋጮ መንግሥታቸው የሚያስብላቸው ግልጽ መብትና ግዴታ ይታወቃል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ይህ የኮርፖሬት አስተሳሰብ
ገና አልተጀመረም፡፡ ስለሆነም፣ የሕዝቡና የአካባቢ ጠንቅ በሆኑ ሥራዎች ላይ የተሰማሩ “ባለሀብቶች” የፈለጋቸውን ጎጂ ተግባር
ፈጽመው፣ ለመለስ ፋውንዴሽን እጅ-መንሻ አቅርበው እንደፈለጉ እንዲሆኑ በር ይከፍታል፡፡ ስለዚህም፣ ከመዋጮው በፊት የኮርፖሬቶች
መዋጮን በተመለከተ፣ ምክር ቤቱ “በነካ እጁ” ሌላ አዋጅ በአፋጣኝ ማውጣት አለበት፡፡ አለበለዚያ፣ ደንበኛ የሚስናና የጭቦ በር
ከፍቶ እንደተወ ሊያውቀው ይገባል፡፡
ተያይቀውም የሚነሱ ጥያቄዎች
አሉ፡፡ “ለመሆኑ የዚህ ድርጅት የበላይ ጠባቂ የሚሆነው ማነው? ድርጅቱ በሥሩ የሚያስተዳድራቸው ድርጆቶች ምን ያህል ይሆናሉ?
ወይስ እንደተባለው ቤተ-መጽሐፍት፣ ሙዚየምና መናፈሻ ብቻ ናቸው? (ይኼ ከሆነ ደግሞ በአዲስ አበባ፣ በባሕርዳር በመቀሌና
በአዋሳ ካሉት የሰማዕታት ድርጅቶች በምኑ ሊለይ ነው? (ሃውልት ባለማቆሙ፣ እንዳይባል ገና ለይቶ-አለየለትም፡፡) በጎ አድራጎት
ድርጅቱ የሚሠጡትን ንብረቶች በምን ሁኔታ ይቀበላል? በመንግሥታዊ ያልሆኑ (መያዶች) አዋጅ ስር ይተዳደራል እንዳይባል፤ ድርጅቱ
ራሱ በአዋጅ የተቋቋመ ነው፡፡ ስለዚህም ቀደም ብሎ የወጣው የመያዶች አዋጅ አይመለከተውም ማለት ነው፤ ወይም እንዳይመለከተው
ተደርጎ ተረቋል፡፡
ሁለተኛው ጥያቄ ደግሞ፣
“ፓርላማው ለምን የመለስን በጎ አድራጎት ድርጅት ብቻ ለማወጅ ፈለገ?” የሚል ነው፡፡ እዚህ ላይ ተያያዥ ጥያቄዎችም አብረው
ይነሣሉ፡፡ ለምሳሌ፣ “ድርጅቱ እንዲቋቋም የገፋፉት ሰዎች እነማን ናቸው? የቤተሰቦቻቸውስ ሚና (መዋጮ ከማዋጣት ባሻገር) እሰውከምን
ድረስ ነው? ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትርስ የበጎ አድራጎት ድርጅት የማቋቋም ፍላጎት ነበራቸው ወይ? ከነበራቸውስ፣ ለድርጅቱ መቋቋሚያ
ምን ተናዘዙ? ወዘተርፈ…” የሚሉ ጥያቄዎችን ያስነሳል፡፡ ከሁሉም
ከሁሉም ግን፣ ፓርላማው በእርግጥ በአንድ ግለሰብ ስም፣ የበጎ አድራጎት ድርጅት ለማቋቋም አዋጅ የማወጅ ሥልጣንና ኃላፊነትስ
አለውን? የሚለውን መዝማዥ ጥያቄ ያስነሳል፡፡ በርግጥም የለውም፡፡ ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም፡፡ ታዲያን፣ የአቶ መለስ
አድናቂዎችና ቲፎዞዎች ሌላ ጓደኛቸውን የሚዘክሩበት መንገድ ቢፈልጉ ይሻላቸው ነበር፡፡ ሆኖም፣ ሩጫቸው ፈሩን ለቆ በዝግ ስብሰባ
አዋጅ እስከማጽደቅ አደረሳቸው፡፡ ያሳዝናል፡፡

ወታደራዊ ደርግ በ1970ዓ.ም በአዋጅ “የአብዮታዊት ኢትዮጵያን ሕጻናት ማሳደጊያን” ዝዋይ
ላይ፤ “የአብዮታዊት ኢትዮጵያን ጀግኖች አንባን” ደብረ ዘይት ላይ (የዛሬውን የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ግቢ ነው)፤ “የጉለሌ
ሕፃናት ማሳደጊያን (ኋላ የሚኪ ሊላንድ ሕጻናት አንባ ተብሎ ነበር) እና በደሴ፣ በኤርትራና በጎዴም የሕጻናት ማሳደጊያዎችን በአዋጅ
አቋቁሞ ነበር፡፡ የበላይ ጠባቂውም ጓድ ሊቀመንበር መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ነበር፡፡ ብዙዎቹ ዝዋይና ጉለሌ ሕጻናት አንባዎች ውስጥ
ያደጉት ልጆች ያባታቸው ስም መንግሥቱ ኃይለ ማርያም እንዲሆንም ይደረግ ነበር፡፡ እነዚህ የ“የአብዮታዊት ኢትዮጵያ” በጎ አድራጎት
ድርጅቶችም በጀታቸውን በቀጥታ የሚያገኙት ከመንግሥት ካዝና ነበር፡፡ ሁሉንም፣ የ“የአብዮታዊት ኢትዮጵያ” የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፣
ደርግ መራሹ የወያኔ/ኢሕአዴግ መንግሥት ያለአዋጅ በተናቸው፡፡ እስከ1997ዓ.ም ድረስ ሲጓተት የቆየው የጉለሌ ሕጻናት ማሳደጊያም
ሴቶቹን ወደቀጨኔ፣ ወንዶቹንም ወደከነማ ሕጻናት ማሳደጊያዎች አዛውሮ ሲያበቃ በለሆሳስ ተዘጋ፡፡

ስለየዳይሬክተሮች
ቦርድ ከአንቀጽ 18-29 ድረስ ሲያትት፣ ስለየበላይ ጠባቂዎችም ቦርድ አቋቋምና ኃላፊነት በተመለከተ ከአንቀጽ 30 – 33 ባሉት አናቅጽት ሥር በዝርዝር አስቀምጧል፡፡ ከሁሉም
በላይ፣ የበጎ አድራጎት ቻርተሩ (የአደራ መስጫ ሰነዱ) ሚስጢራዊ አልነበረም፡፡ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ታትሞ ወጥቷል፡፡ ከታኅሣሥ
15 ቀን 1952ዓ.ም ጀምሮም አዋጁ ተፈፃሚ እንደሆነ በግልጽ ደንግጓል፡፡ ለምን “ግልጽነታችንና ተጠያቂነታችን እያደር እያሽቆለቆለ” እንደሄደ ያሳብቃል፡፡ በተጨማሪም፣ የምናቋቁማቸው ድርጅቶች ርዕይና ዓላማም
ምን ያህል እየኮሰሱ እንደሔዱ ደህና አድርጎ ያሳያል፡፡ የጽናት፣ የበጎ ፍቃድ ማጣትና የጥድፊያ ነገር ምንያህል ቀልበ-ቢስ እንዳደረገንም
የቻርተሩን መግቢያ ብቻ ማንበቡ ይጠቁማል፡፡
እንዲህ ይላል፤
“ሞዓ አንበሳ ዘእነገደ ይሁዳ፤ እኛ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ፣ ሥዩመ እግዚአብሔር ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ፤ ለመጣቶች፣ ለሽማግሌዎች፣
ለሕመምተኞች፣ ለአካለ ስንኩሎች፣ የአካል ወይም የምግባር ተሐድሶ ለሚያሻቸውና የገንዘብ ዐቅማቸው የማይፈቅድላቸው ከመሆኑ የተነሣ
ከችሎታቸው ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ትምህርት ለማግኘት ለተሳናቸው ሰዎች በሚደረገው እርዳታና በትምህርት፤ በሳይንስና በሥነ ጥበብም
መስፋፋት ረገድ የሚያሳየው አርአያነት ለሕዝብ አስፈላጊ፤ ለአገርም ጠቃሚ በሚሆኑት ነገሮች ሁሉ ቀዳሚና አበረታች በመሆን ለምንወዳት
ኢትዮጵያ ጽኑ ኃይልንና ምግባራዊ መሪነትን የሚሠጥ፤ እንደዚሁም ደግሞ እኛም የምንወደውን የሕዝባችንን ደኅንነትና የእድገት እርምጃ
ለማጎልመስ በሕይወታችን ዘመን ለፈጸምነው መሥዋዕትነትና ጥረት ዘላቂ መታሰቢያ የሚሆን አንድ የበጎ አድራጎት ድርጅት ለማቋቋም አስበን፤
ቀጥሎ ያለውን ቻርተር (የአደራ መስጫ ሰነድ) እንዲወጣ አዘናል፡፡” ይላል፡፡ ምን ጭማሪ ያስፈልገዋል?! ራሱን በራሱ ገላጭ ነው፡፡
በዚህ ቻርተር መሠረት ተቋቁሞ
ለአስራ አምስት ዓመታት ያህል ሢሠራ ከቆየ በኋላ፣ በወርኃ ጥቅምት 1967ዓ.ም ጊዜያዊ ታደራዊ አስተዳደር ደርግ፣
መመሪያውን ሶሻሊዝም ባደረገ ሰሞን፣ የቀ.ኃ.ሥ በጎ አድራጎት ድርጅትንም “ለሕዝብ ጥቅም” በሚል ሽፋን፣ በአንድ የመሰቀጥጥ ማርሽ
በታጀበ አዋጅ ወረሰው፡፡ ያ፣ ታላላቅ የሀገርና የአኅጉር አርኣያነት ያላቸውን ግለሰቦችና ድርጅቶች ሲያበረታታ የነበረው የቀዳማዊ
ኃይለ ሥላሴ ፌሎውሺፕም አብሮ ከሰመ፡፡ ይኼው እስከዛሬም ድረስ ኢትዮጵያውያን የታወቀና የታመነ፣ ባለሙያዎችናና የሀገር ባለውለታዎችን
የሚሸልምና የሚያበረታታ ድርጅት ሳይኖራት ሰላሣ ስምንት (38) ዓመታት ነጎዱ፡፡ ደርግ፣ የአፍሪካውያን የኖቤል ሽልማት ተፎካካሪ
ይሆናል ተብሎ ተስፋ የተጣለበትን እንድ ብሩሕ ድርጅት፣ ዐይነ-ስቡን አጠፋው፡፡ (ከዚያም፣ በስልጣን ሰክሮ አቀብ-ቁልቁል ሲል ኖሮ፣
ራሱን-በራሱ አጠፋ፡፡ “አይ የንትን ችኩል ነገር፣ ካላጣው ሥጋ ቀንድ ይነክሳል” አሉ! (ደህና ሰንብቱ!)
በሳምናታዊው የአዲስጉዳይ መጽሔት ቅጽ 7፣ ቁ. 148 ላይ፤ በጥር 18 ቀን 2005 ዓ.ም የወጣ
Editor's Note:
The Biased and TPLF affiliated Reporter Newspaper has
published the following article after AddisGuday /አዲስጉዳይ/ Megazine published the above article on January 26, 2013. This is an indication for the unwise decision taken by the Parliament. We still insist the Parliament and the Standing Committee of Legal Affairs in the Parliament to investigate and/or revise its Proclamation for the benefit of the Parliament. Otherwise, it will be a disaster for the parliament and the representatives by echoing how they worship the late Meles Zenawi.
If you want to verifay the news Click here:
http://ns.ethiopianreporter.com/index.php/news/item/541-%E1%8B%A8%E1%88%98%E1%88%88%E1%88%B5-%E1%8D%8B%E1%8B%8D%E1%8A%95%E1%8B%B4%E1%88%BD%E1%8A%95-%E1%8A%A8%E1%88%98%E1%8A%95%E1%8C%8D%E1%88%A5%E1%89%B5-%E1%89%A0%E1%88%9A%E1%88%98%E1%88%A8%E1%8C%A1%E1%8A%93-%E1%8A%A8%E1%89%A4%E1%89%B0%E1%88%B0%E1%89%A6%E1%89%BB%E1%89%B8%E1%8B%8D-%E1%89%A0%E1%88%9A%E1%8B%88%E1%8A%A8%E1%88%89-%E1%8A%A0%E1%89%A3%E1%88%8B%E1%89%B5-%E1%8B%AD%E1%88%98%E1%88%AB%E1%88%8D
30 January 2013 ተጻፈ በ ዮሐንስ አንበርብር
የመለስ ፋውንዴሽን ከመንግሥት በሚመረጡና ከቤተሰቦቻቸው በሚወከሉ አባላት ይመራል
• መሣርያዎችንና ተሽከርካሪዎችን ከቀረጥ ነፃ ያስገባል
• ከውርስና ስጦታ በተጨማሪ የመንግሥት ድጐማ የፋውንዴሽኑ ገቢ ይሆናል
• ከውርስና ስጦታ በተጨማሪ የመንግሥት ድጐማ የፋውንዴሽኑ ገቢ ይሆናል
የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አሻራን ለመዘከርና ለትውልድ የማስተላለፍ ኃላፊነት የተሰጠው የመለስ
ፋውንዴሽን፣ ከቤተሰቦቻቸው በሚወከሉ አራት አባላትና ከጠቅላላ ጉባዔው በሚመረጡ ሰባት የመንግሥት ተወካዮች በቦርድ
እንደሚመራ ታወቀ፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሳምንት በፊት ባካሄደው ስብሰባ ፋውንዴሽኑን ለመመሥረት የሚያስችል አዋጅ ያፀደቀ መሆኑን ሪፖርተር መዘገቡ ይታወሳል፡፡ ይሁን እንጂ ምክር ቤቱ ባልተገለጸ ምክንያት ጋዜጠኞች አዋጁን ለማፅደቅ የተደረገውን ሥነ ሥርዓት እንዳይከታተሉ በማድረጉ ዝርዝር ጉዳዮችን ለማቅረብ አልተቻለም፡፡
ዝግጅት ክፍላችን ባደረገው ጥረት የፀደቀውን አዋጅ ረቂቅ ማግኘት ተችሏል፡፡ አዋጁ አራት ምዕራፎችንና ሃያ አራት አንቀጾችን የያዘ ሲሆን፣ ፋውንዴሽኑ ከ60 በላይ የሚሆኑ አባላትን የያዘ ጠቅላላ ጉባዔ እንደሚኖረውና ይህም ጉባዔ ፋውንዴሽኑን በሚመለከቱ ጉዳዮች ከፍተኛ የውሳኔ ሰጪ አካል እንደሚሆን ይደነግጋል፡፡
የፋውንዴሽኑን ዓላማ የማስፈጸም፣ የመምራትና የመወከል ሥልጣን ደግሞ 11 አባላት ለሚኖሩት የፋውንዴሽኑ ቦርድ ሰጥቷል፡፡ የፋውንዴሽኑ ጠቅላላ ጉባዔ ከአቶ መለስ ዜናዊ ቤተሰብ የሚወከሉ አራት አባላት፣ ከመከላከያ ሠራዊት የሚወከሉ ሦስት አባላትና ከሁሉም ክልሎች የሚወከሉ አምስት አምስት አባላት ይኖሩታል፡፡
በተጨማሪም ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት፣ ከውጭ ጉዳይ፣ ከትምህርት፣ ከጤና ጥበቃ፣ ከመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት፣ ከቅርስ ጥናትና ጥበቃ ሚኒስቴር መሥርያ ቤቶች ባለሥልጣን ከወጣቶችና የሴቶች ማኅበራት አንድ አንድ አባላት የሚወከሉበት ሲሆን፣ የመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሦስት ተወካዮችም የጠቅላላ ጉባዔው አባላት እንደሚሆኑ አዋጁ ይደነግጋል፡፡
ጠቅላላ ጉባዔው የፋውንዴሽኑ ከፍተኛ ውሳኔ ሰጪ አካል ከመሆኑ ባሻገር፣ ከአባላቱ አሥራ አንድ የቦርድ አባላትን በመምረጥ ፋውንዴሽኑን እንዲመሩ ያደርጋል፡፡ ከቦርዱ አባላት መካከል አራቱ ከአቶ መለስ ቤተሰብ እንደሚመረጡ የሚደነግግ በመሆኑ፣ የጠቅላላ ጉባዔው አባላት የሚሆኑት አራቱ የአቶ መለስ ቤተሰቦች በቀጥታ የቦርድ አባላት እንደሚሆኑም ለመረዳት ይቻላል፡፡
ቀሪዎቹ ሰባት የቦርድ አባላትም ከጠቅላላ ጉባዔው የሚመረጡ ሲሆን፣ የሥራ ዘመናቸውም ለአራት ዓመታት እንደሚሆን ነገር ግን ለቀጣይ የአገልግሎት ዘመናት መመረጥ እንደሚችሉ አዋጁ ይገልጻል፡፡ የቦርድ አባል በሚሆኑት አራቱ የአቶ መለስ ቤተሰቦች የአገልግሎት ዘመን ግን አዋጁ የሚለው ነገር የለም፡፡
ቦርዱ የፋውንዴሽኑን ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንት የመምረጥ፣ የፋውንዴሽኑን የሥራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር የመሾምና የማሰናበት ኃላፊነትም ተሰጥቶታል፡፡
ለሥራ አስፈጻሚ ዳይሬክተሩ ተጠሪ በሚሆኑ የሥራ መደቦች ላይ የሚመደቡትን ኃላፊዎች ሹመት ያፀድቃል፣ ጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ በማይኖርበት ጊዜ የጉባዔውን ውሳኔ በሚሹ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ በመስጠት በሚቀጥለው ስብሰባ እንዲያፀድቅ እንዲሁም የፋውንዴሽኑን የውስጥ ደንብና የራሱን መመርያ እንዲያወጣና ለፋውንዴሽኑ ማስፈጸሚያ የሚውል ገንዘብ የሚሰበሰብበትን ስልትና አጠቃቀሙን እንዲወስን በአዋጁ ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡
የፋውንዴሽኑን የገቢ ምንጮች በተመለከተም ዋና ዋናዎቹ ከመንግሥት ከሚሰጥ ጠቅላላ ወይም የፕሮግራም ድጐማ፣ ከውርስ፣ ከስጦታና ከዕርዳታ የሚገኙ ገንዘብና ንብረቶች እንደሚሆኑና ልዩ ልዩ የገቢ ማስገኛ እንቅስቃሴዎችና ሌሎች ምንጮች የተቋሙ የገቢ ምንጭ እንደሚሆኑ ያስረዳል፡፡
ፋውንዴሽኑ ለሥራ ማስፈጸሚያ ወደ አገር የሚያስገባቸው ዕቃዎች፣ መሣርያዎችና ተሽከርካሪዎች ከቀረጥና ታክስ ነፃ እንደሚሆኑ ይደነግጋል፡፡ የአቶ መለስ ዜናዊ አስክሬን የሚያርፍበትንና በሕዝብ የሚጐበኝ መናፈሻ መገንባትና ማስተዳደር፣ አቶ መለስ የጻፏቸው መጽሐፎችና የተለያዩ ጽሑፎች፣ እርሳቸውን የተመለከቱ ጥናታዊ ፊልሞች፣ ምስል፣ ድምፅና የመሳሰሉትን የሚገኙበትና ጥቅም ላይ የሚውሉበት ቤተ መጻሕፍት ማቋቋም ከፋውንዴሽኑ የሚጠበቁ ተግባራት ናቸው፡፡
በኢኮኖሚያዊ ማኅበራዊ ልማት፣ በዲሞክራሲ፣ በሰላምና በኅብረተሰብ ለውጥ አስተሳሰብና ተዛማጅ መስኮች ለሚደረጉ ጥናቶች ድጋፍና ሁኔታዎችን ማመቻቸት፣ እንዲሁም በዚህ ተግባር ላይ የላቀ አስተዋጽኦ ለሚያበረክቱ ሰዎች ሽልማት መስጠትም የፋውንዴሽኑ ሌላኛው ተግባር ይሆናል፡፡
በችግር ምክንያት ትምህርታቸውን ለመከታተል ለማይችሉ በተለይም ለሴቶች ነፃ የትምህርት ዕድል መስጠት፤ አቅም በፈቀደ መጠንም ለውጭ አገር ዜጐች ተመሳሳይ ዕድል እንዲሰጥም በአዋጁ ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡
ከጠቅላላ ጉባዔው አባላት መካከል ሁለት ሦስተኛ የሚሆኑት አዋጁ እንዲሻሻል ከተስማሙ ለመንግሥት ቀርቦ ሊሻሻል እንደሚችልም ተደንግጓል፡፡

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ
Thanks a lot for your comments.