ተቃዋሚዎች ሆይ፤ ተባበሩ!
(ከፍቷልና ችግሩ)
በሰሎሞን ተሰማ ጂ. semnaworeq.blogspot.com
“በኔ የምርጫ ወረዳ
ውስጥ ማናባቱ ነው ሊወዳደደር የሚከጅለው!” እስከማለት የደረሱም አሉ፡፡ አስተያየታቸውም ሆነ አመለካከታቸው የደጅአዝማችነት ነው፡፡
በኔ ደጅ ድርሽ ትሉና አለቃችሁም የሚል ጩኸትና ቡራ ከረዩ አለበት፡፡
በዚያም ላይ ድምጽን እንደቀድሞዎቹ የመሬት ከበርቴዎች ለብቻቸው ለመቀራመትና “የተከበሩ አቶ እከሌ ወይም ፕሮፌሰር እከሌ ወይም
ዶክተር እከሌ” ለመባል ብቻ ነው የሚፈልጉት፡፡


ስጋታችን ግልጽ ነው፡፡ ባለፉት ሁለት ብሔራዊ ምርጫዎች ዋዜማና ማግሥትም የነበሩት ከባድ
ፈተናዎች በሁለት የተከፈሉ ነበሩ፡፡ አንደኛው ሰበብ፣ የፓርቲዎቹ ውስጣዊ ነውጥ ውስጥ መግባት ነበር፡፡ በሁለተኛ ደረጃም የሚመጣው
ውጫዊ የሆነውን ጫና ለመቋቋም አለመቻላቸው ነው፡፡ ውጫዊዎቹ ግፊቶች ከገዢው ፓርቲና ከሌሎች የተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዲሁም ከዲያስፎራው
በኩል የሚመጡ ናቸው፡፡ ገዢው ፓርቲ ልዩ ልዩ ማዳከሚያዎችን እንደሚጠቀም ያደባባይ ሚስጢር ስለሆነ ወደሌሎቹ እንለፍ፡፡ ከሌሎች
ተቃዋሚዎችም ጋር የሚስተሳስሯቸው ጉዳዮች ይልቅ የሚያለያዩዋቸው በጣም ጥቂት ናቸው፡፡ ሆኖም፣ በጋራ ከሚያስማሟቸው ነገሮች ይልቅ
የሚያለያዩዋቸውን ጉዳዮችን ማራገቡ የማን ስራ እንደሆነም እናውቀዋለን፡፡ በብዛት ስልጣናቸውን የሙጥኝ ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲ ጉምቱ
መሪዎች ትግባር መሆኑን መናገር ያስፈልጋል፡፡
መንግስታዊዎቹም ሆኑ የግሎቹ የመገናኛ ብዙኃን ከዚህ አልፈህ አትሂድ ወይም እዚህ ድረስ
ብቻ አስብ እየተባሉም እንደሚሠሩ እሙን ነው፡፡ ስለሆነም፣ ዲሞክራሲያዊ የሆነ ሥርዓት ለመገንባት ካስፈለገ፣ በመጀመሪያ ዲሞክራሲውን
ሊሸከሙ የሚችል ትከሻና አደረጃጀት ያላቸው ተቋማት ያስፈልጋሉ፡፡ (ታዲያን፣ የተቃዋሚ ፓርቲዎቹንም ጨምሮ ነው፡፡) የማዘጋጀቱ ሥራ
ከምርጫ ቦርድ መጀመሩም እሰየው የሚያሰኝ ነው፡፡ ከዚያም ወደሌሎቹ ተቋማት እንደሚንሰራፋ ጥርጥር የለንም፡፡ በተለይም፣ የመገናኛ
ብዙኃኑን ገለልተኝነት በተመለከተና የፖሊስና የፀጥታው እንዲሁም የሠራዊቱንም ገለልተኝነት በተመለከተ አሌ የማይባል የጋራ አጀንዳ
ቀርፆ መንቀሳቀስ ያዋጣል፡፡ ካለፉት ብሔራዊና ክልላዊ ምርጫዎች ብዙ ተመክሮዎችን ማግኘታችን መካድ የለበትም፡፡ ስሕተቶቹን አርሞ፣
ጥንካሬዎቹንም ጠብቆ መዝለቅ ከፓርቲዎቹ ይጠበቃል፡፡ በተለይም ከተቃዋሚዎቹ በኩል የግድ ያስፈልጋል፡፡

ያም ሆኖ፣ በተወሰኑት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች አካባቢ ከባድ የአመለካከት ችግሮች እንዳሉ
ልንገልፅ እንወዳለን፡፡ ዋና ዋናዎቹም ችግሮች የሚከተለት ናቸው፡፡ አንደኛ፣
የድምፅ ከበርቴነት አስተሳሰብ ነው፡፡ ይህ ስሜት በብዙዎቹ ላይ ከ1980ዎቹ ጀምሮ የሚታይ አስተሳሰብ ነው፡፡ በተለይም፣
በብሔር በተደራጁት የፓርቲ አመራሮች አካባቢ በጣም ይንፀባረቃል፡፡ ላለፉት አስራ ስምንት አመታት ካለነሱም ሌላ ወኪል መሪዎቹ በሚወዳደሩበት
አካባቢ/ወረዳ የሌለ ይመስል በየምርጫው ወቅት ከረቫታቸውን አስረው የሚታበዩት ብዙ ናቸው፡፡ ይባስ ብሎም፣ “በኔ የምርጫ ወረዳ
ውስጥ ማናባቱ ነው ሊወዳደደር የሚከጅለው!” እስከማለትም የደረሱ አሉ፡፡ አስተያየታቸውም ሆነ አመለካከታቸው የደጅአዝማችነት ነው፡፡
በኔ ደጅ ድርሽ ትሉና አለቃችሁም የሚል ጩኸትና ቡራ ከረዩ አለበት፡፡
በዚያም ላይ ድምጽን እንደቀድሞዎቹ የመሬት ከበርቴዎች ለብቻቸው ለመቀራመትና “የተከበሩ አቶ እከሌ ወይም ፕሮፌሰር እከሌ ወይም
ዶክተር እከሌ” ለመባል ብቻ ነው የሚፈልጉት፡፡ ሕዝቡ ላለፉት 18 ዓመታት የተካሄዱትን ነገሮች ልብ ብሎ ያጤናቸው መሆኑን አንኳን
አያገናዝቡትም፡፡
በገዢው ፓርቲም አካባቢ ያለው ሕመም ይኼው ነው፡፡ በቅርቡ ነው የአቶ መለሠ ዜናዊ ምትክ
ማን መሆን እንዳለባቸው የታወቀው፡፡ አለበለዚያ፣ አቶ መለሠ በጥርስ ብቻ ሳይሆን በድዳቸውም ጭምር በወረዳቸው እንደፈለጉ እንዲመረጡ
ልዩ መብት የተሰጣቸው ነበር እሚመስለው፡፡ በተቃዋሚውም አካባቢ ያው ነው፡፡ ከኛ ወዲያ ላሳር የሚሉት ናቸው የሚበዙት፡፡ የመተካካት
ፈሩን ከቶም አልጀመሩትም፡፡ ሊጀምሩትም ያሰቡት በቁጥር ከእጅ ጣት አይበልጡም፡፡ ወደፊትም ቢሆን በጥርሳቸውም ሆነ በጥፍራቸው፣
የሕዝቡን የተባበሩ ጥሪ ከመቦጫጨቅ የሚመለሱ አይደሉም፡፡ የእነርሱን የድምጽ ከበርቴነት ማን ወንድ ነው የሚፈታተናት? ምናባቱስ ቆርጦት፡፡ ስለሆነም
የሕዝቡን የተባበሩ ወይም ተሰባበሩ ጥሪ ጆሮ ዳባ ልበስ የሚያሰኛቸው ይኼ “የድምፅ ከበርቴነት” አጉል አምልኮ መሆኑን ልንናገር
እንወዳለን፡፡

በሦስተኛ ደረጃ የሚስተዋለውን የሀገር ውስጥ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ችግር እናንሳ፡፡ ይህ ችግር በዋናነት ጊዜውን ያለመረዳት ችግር ነው፡፡ ጊዜው እንደተረዳነው ከሆነ የብሔረተኝነትና የጎሰኝነት
ዘመን አይደለም፡፡ ሆኖም ግን ብዙዎቹ የፓርቲ አመራሮች ይኼንን ያከተመ ዘመን በቅጡ አልተረዱትም፡፡ ሊረዱትም አይፈልጉም፡፡ ምክንያቱም
ስልጣናችንን ያሳጣናል ብለው ስለሚሰጉና ያንንም ላለማጣት ሲሉ ነው፡፡ እርግጡን ለመናገር ግን ኢትዮጵያ ውስጥ የብሔረተኝነት ችግር
ማክተሙን የሚያሳዩ ሦስት ምልክቶች እንጠቅሳለን፡፡ የመጀመሪያዎቹ ምልክት የ1997ቱና የ2002ቱ ምርጫዎች ውጤት ነው፡፡ በነዚህ
ምርጫዎች በድምር/በጅምላው ከብሔር ድርጅቶቹ ይልቅ ሕብረ-ብሔራዊዎቹ ቅንጅትና መድረክ ከፍተኛ ድምፅ አግኝተዋል፡፡ በጠራራ ፀሐይ
እንደተዘረፈ በሚታወቀው የ1997ቱም ምርጫ ሆነ በወከባና በሸፍጥ በተጠናቀቀው የ2002ቱ ምርጫዎች እንደታየው ከሆነ የብሔር ፓርቲዎች
ከንግዲህ ወዲያ “ጤናችሁን ይስጣችሁ!” ወይም በኦሮሚኛ “ፈያ ደይ!” ተብለዋል፡፡ በቂ ማሳያ ነው፡፡ ሁለተኛው ምልክት ደግሞ፣
ብዙ ጊዜ በጽንፈኝነት የሚታሙት ፓርቲዎች ከሕብረብሔር ድርጅቶቸ ጋር ለመሥራት ያሳዩት ተነሳሽነት ነው፡፡ ኦፍዴን-ከቀድሞው ሊቀመንበር
አቶ ቡልቻ ደመቅሳ መጣጥፎች እንደምንረዳው ከሆነ፣ ብሔረተኛነቱን ሊያነሳ አፍታ ብቻ ነው የቀረው፡፡ ይበል የሚያሰኝ እርምጃ ነው፡፡
በውጭም የኦነግ አመራር ያሳየው ሆደ ሰፊነት በቀላሉ የሚታይ ምልክት አይደለም፡፡ የአረናም ቢሆን የሚያስመሰግን ምልክት ነው፡፡
በሦስተኛ ደረጃም የምንጠቅሰው ምልክት የእስልምና ተከታይ ወንድሞቻችና እህቶቻችንን የብሔረተኛነትን ግንብ ተሻግሮ የመነሳት
ምልክት ነው፡፡ ትልቅ ምልክት ነው፡፡ ሰው በግል መብቱ ከመጡበት የብሔርና የጎጥ አጥር እንደማይከልለው ማሳየት ችሏል፡፡ በዓይነቱም
ሆነ በይዘቱ የብሔር ፖለቲካን መቅኖ ያሳጣ ተግባር ነው፡፡ ትልቅ ማነቃቂያ ደወል ነው - ለገዢው ፓርቲም ሆነ ለተቃዋሚዎቹ፡፡ በኢትዮጵያ
ውስጥ ከታዩት የትግል ስልቶችም ሁሉ በይዘቱ ከፍ ያለ ነው፡፡ ከአርባ አምስት አመታት ወዲህ፣ የብሔረተኝነት አደጋን ተሻግሮ ወደሰውነት
ደረጃ የደረሰ ትግል ከተባለም በዋናነት መጠቀስ እንደሚችል እንተማመናለን፡፡

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ
Thanks a lot for your comments.