Amhara National Democratic Movement Members Letter to Minster Bereket Simon.
Here is a letter from ANDM (Amhara National Democratic Movement) Members in Bahir Dar. They wrote it to Communication Minster Berket Simon. Their Letter is touching. They seem highly careful and conscious. Obviously, they are addressing both Bereket Simon and the wider public in nude words. I have posted the original letter and its link on semnaworeq.blogspot.com for the wider readers who don't have the access and the means for proxy links.
If you are here in Ethiopia, please read the detailed message below.
Regards,
Solomon Tessema G.
Editor and blogger of semnaworeq.blogspot.com
Addis Ababa, Ethiopia.
1
ይድረስ ለክቡር አቶ በረከት ስምዖን
በመጀመሪያ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችንን ክቡር አቶ መለስ ዜናዊን ባልታሰበና ድንገተኛ በሆነ መንገድ በአጣንበት ዓመት ማግስት ላይ ሆነን ይህንን ጫፍ የወጣና ሃይ ባይ ያጣን የአደረጃጀት ችግርና የሙስና ድርጊት ስናጋልጥ በእንቁ መሪያችን መለየት በተሰማን መሪር ሃዘን ከተሰበረው ልባችን በላይ ደግሞ በየቀኑ በክልላችን በተለይም በባህር ዳር ከተማ አየተፈፀመ ያለው ህገወጥ አሰራርና የተፈጠረው የዝርፍያና የአፈና መዋቅር እያደረሰ ያለው በደልም በጣም እያንገሸገሸን በመሆኑ ክቡርነትዎም ሆኑ ሌሎች ውድ ታጋዮቻችን ዛሬም እንደትላንቱ የበረሃው ፍልሚያ ሳትሰለቹ በፅናት በማታገልና በመታገል ይህንን እሾህና አሜኬላ ለመመንጠር ብርታትና ሃይል ትሆኑናላችሁ፣ ከዚህ ጥቆማ በመነሳት ነገ ከነገ በኋላ በግንባር ትግል ለማድረግም ምቹ ሁኔታና እድል ትፈጥሩልናላችሁ በሚል እምነትና ወኔ ነው ጥቆማውን የምናቀርበው። ጠንካራ ድርጅትና መንግስት ባለበት አገር እንድህ ዓይነት የማን አለብኝነትና የጋጠወጥነት ስራ እየተሰራ ዝም መባሉ በእነት እርዓቱን አደጋ ላይ የጣለ ተግባር መሆኑን ከማንም በላይ ለእናንተ ማስረዳትም ሆነ መንገር የሚያሻው ጉዳይ ነው ብለን ባንወስድም ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው እንደሚባለው እነፋንታ ደጀን በብልጣብልጥ አካሄዳቸው የቀን ታጋይ የማታ አታላይ ሁነው ህዝቡንና አባሉን እየጎዱት በመሆኑ ብሶታችንን ለመግለፅና መፍትሄም ለመሻት ይህንን መረጃ ለመላክ ተገድደናል። ስለሆነም መረጃው /ኢንፎርሜሽን/ በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ውስጥ በእነፋንታ ደጀንና ሌሎች አንዳንድ የክልሉ አመራሮች የበላይ ጠባቂነትና መሃንዲስነት የድርጅታችንን መርህና የአሰራር ስርዓት ባልተከተለ መንገድ እየተፈጠረ ያለውን ህገወጥ አደረጃጀትና ቡድንተኝነትን ለመጠቆምና ለትግሉ መለኮሻ ይሆናል በሚል እንጅ ዋናው መረጃ በመድረክ /ግንባር/ በሚደረገው ትግልና እናንተም በምታደርጉት ክትትል በተሟላ መንገድ ሊገኝ የሚችል መሆኑን እየጠቆምን በአሁኑ ሰዓት የከተማችን የድርጅትና የመንግስት ስራዎች በእውሸት ተቀናብረው ከሚተላለፉት ሪፖርቶች ባሻገር ባሉበት የቆሙበት ሁኔታም እንዳለ የክልሉን አመራር ጨምሮ ሁሉም የሚያውቀው ነው። በሌላ በኩል ክቡር ከንቲባው ለዚህ ላደራጁት የዝርፍያ ቡድን አባላት ሰሞኑን አምስት Dx የቤት መኪና አስገዝተው ለማከፋፈል በዝግጅት ላይ ሲሆኑ በተቃራኒው ደግሞ በዙሪያ ቀበሌዎች የሚገኘው አርሶአደር ምንም ዓይነት የመሰረተ ልማት ግንባታ አልተሰራልንም እያለ ሲጮህ ባጀት የለንም በሚል ምላሽ ሲሰጥ እንሰማለን፤ በዚህም የከተማው ህብረተሰብ እየተገረመ ይገኛል፤ ለልማት ሳይሆን ለቅንጦት ቅድሚያ የሚሰጥ አመራር በመኖሩ። ታዲያ የክልላችን አመራሮች ይህንን እያዩ እንዳላዩ ማለፋቸው ምን ይባላል!?
I. በከንቲባውና በአቶ ፋንታ ደጀን አማካኝነት አሁንም ድረስ በርካታ ወንጀሎች እየተፈፀሙ ናቸው
♦ በ2004 በተደረገው የፀረ ኪራይ ሰብሳቢነት ትግል ወቅት አቶ ሰማቸው ወንድማገኘው ያለአግባብ በተለያዩ እህቶቹና ወንድሞቹ ስም /ምንም የሀብት መሰረት በሌላቸው ሁለት እህቶቹና አንድ የጎዳና ተዳዳሪ ወንድሙ ስም የገዛቸው ሁለት ኮንዲሚኒየም ቤትና የሰራቸው ሁለት ቪላ ቤቶች፣ እንዲሁም በደብረታቦር ከተማ ውስጥ በራሱ ስም አንድ ቤት እያለው በተሳሳተ መረጃ ማለትም ደብረታቦር ከተማ አመራር እያለ 200 ካ.ሜ ቦታ ወስዶ እያለ በተመሳሳይ ሁኔታ በባህርዳር ከተማ የግሽ አባይ ቀበሌ ነዋሪ ነኝ በሚል በተጭበረበረ መንገድ መታወቂያ አውጥቶ አቅም የሌለው በሚል ተመዝግቦ በአቅም መገንባት በሚል ባህርዳር ከተማ አስተዳደር ህዳር11 ቀበሌ በ10 ብር ሂሳብ 200 ካ.ሜ ቦታ ወስዶ የሰራው አንድ ቤት የሚያሳየው ግለሰቡ ያለአግባብ ሀብት ማከማቸቱን ነው በሚል የተደረገውን ግምገማና
2
በከተማ አስተዳደር ደረጃም ከአቶ ባዘዘው ገላው ጋር በመሆን በጥቅም ትስስር ለ18 ግለሰቦች በተለያዩ ማህበራት እንደተደራጁ ተደርጎ ለእያንዳንዳቸው ሁለትና ከዚያ በላይ ቦታ ሰጥተዋል በሚል የተገኘውን መረጃ መነሻ በማድረግ በፀረ ሙስና ኮሚሽን ምርመራ ተጀምሮ የነበረ ቢሆንም በአቶ ፋንታ ደጀን ጫና ምርመራውና ክትትሉ እንዲቆም ተደርጓል። መረጃውን ያጋለጡ ግለሰቦችም አደገኛ በሆነ መንገድ ክትትል እየተደረገባቸው ከመሆኑም ባሻገር በግልፅ እረፉ አየተባሉ የማሳደድ ስራ እየተሰራባቸው ይገኛል።
♦ አቶ ስማቸውና አቶ ፋንታ ደጀን ከእነፋሲል ሙሉና ከእነደጀኔ ሺባባው ጋር በመሆን በአቶ እያሱ ዳምጤ /የደቡብ ጎንደር ተወላጅና የአቶ ፋንታ ደጀን የቅርብ ዘመድ የሆነው/ አማካኝነትና በአቶ አላዩ መኮንን የከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ አመቻችነት በሚፈጥሩት ትስስር ለግንባታ የሚሆን ቀይ አፈር/ሬድ አሽ/ አቶ እያሱ ውክልና ወስዶ ያለምንም ክፍያ ማዕድኑን ወስዶ ለኮንትራክተሮች እንዲሸጥላቸው በማድረግ በርካታ የህዝብና የመንግስት ንብረት ለግል ጥቅማቸው ያውላሉ /ለአብነት ለቴክስታይል ፋብሪካ ማሻሻያ ግንባታ የሚውል ግምቱ 3 ከሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ሬድ አሽ ሽጠው ለግል ጥቅማቸው እያዋሉት ከመሆናቸውም በላይ የተለያዩ የጨረታ ሰነዶችን ከማዘጋጃ ቤት አውጥተው እየሰጡ እሱና ሌሎች ከእሱ ጋር የጥቅም ትስስር ያላቸው ኮንትራችተሮች አለአአግባብ ጨረታውን እንዲያሸንፉ በማድረግ ምዝበራ እየፈፀሙ ይገኛሉ/።
♦ በአቶ ደጀኔ ሺባባው አግባቢነት ከባህር ዳር ሆቴል ባለቤት አቶ በዛብህ ጋር በመሆንም በርካታ የሙስና ስራዎች እየሰሩ ይገኛሉ። በነገራችን ላይ አቶ በዛብህ የአቶ ስማቸው ወንድማገኘሁ አጋቢ ዳኛ ሆኖ ያጋባቸው ሰው ነው።
♦ በተጨማሪም አቶ ስማቸው በወንድም አግማስ ወንድማገኘሁ ስም ቀበሌ 11 አንድ ኮንዲሚኒየም ቤት፣ በቀበሌ 16 ደግሞ ቃል ኪዳን ብዙዓለም በምትባል የእህቱ ልጅ ስም ሌላ ኮንዲሚኒየም ቤትገዝቷል። እነዚህ ወንድሙና የእህቱ ልጅ ምንም መተዳደሪያ ገቢ ሳይኖራቸው እንዴት ቤት በራሳቸው ስም ገዙ የሚለውን ጥያቄ ለመመለስም የምርመራ ስራ መሰራት ያለበት ቢሆንም አቶ ፋንታ ደጀን በሚሰጠው ሽፋን አማካኝነት እየተድበሰበሰ ይገኛል።
♦ በሌላ በኩል ግንቦት 20 ቀበሌ ላይ 3 ቦታዎች በቤተሰቦቹ ስም ወስዶ እንዲሸጥ ያደረገ ሲሆን አሁንም አንድ ቦታ በፓስ ወርድ ታስሮ ሚስጢሩ እንዳይወጣ ታግዷል።
♦ ክቡር ከንቲባው ያለአግባብ ሃብት በተለያዩ የቤተሰቡ አባላት ስምና በራሱ ስም አካብቷል በሚል ክሱ ከተጨባጭ መረጃ ላይ ተመስርቶ በክልሉ የስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አማካኝነት ቢጀመርም አቶ ፋንታ ደጀን /ይህንንም በተመለከተ መረጃውን አቶ ሲሳይ ከተባለው የኮሚሽኑ አቃቤ ህግ በስልክ ቁጥር ... ማግኘት ይቻላል/።
♦ በአሁኑ ሰዓት አቶ ስማቸውን ወደ ክልል ለመሳብና የባህል ቱሪዝምና ፓርኮች ቢሮ ምክትል ሃላፊ አድርጎ ለመሾምና መረጃው ተድበስብሶ እንዲቀር ለማድረግ በአቶ ፋንታ ደጀን አስተባባሪነት ሰፊ ስራ እየተሰራ እንደሆነም መረጃዎች አሉን።
♦ በተጨማሪም የባህርዳር ከተማ አስተዳደር የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ሃላፊ የነበረውና አሁን የሲቪል ሰርቪስ ሃላፊ ሆኖ የተሾመው አቶ ቢያድግልኝ አድምጠው ምንም ግንባታ ሳይካሄድ 2.5 ሚሊዮን ብር ለኮንትራክተር አንዲሰጥ አድርጓል፣ በተጨማሪም በርካታ መጠን ያለው ሲሚንቶና የግንባታ ብረታብረት በሙስና ለግል ጥቅም አውሎታል፣ ሆን ብሎ እንዲበላሽም አድርጎታልና መረጃው ይጣራልን ብለው የጽ/ቤቱ ሰራተኞች በግምገማ በግልፅ ቢያነሱበትም ክቡር ከንቲባው ችግሩን
3
ለመደባበቅና እራሱም የዚሁ ችግር ተጋሪ ስለሆነ /ምክንያቱም ከንቲባው የእህቴ ቤት ነው እያለ ሲያታልልን የነበረውን ቤት ሲያሰራ የተጠቀመው ብረት፣ አሽዋና ሲሚንቶ የተወሰደው ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ማእከላት መስሪያ ተብሎ ከተገዛው ቁሳቁስ ስለሆነ/ የግል ጓደኞቹና የአካባቢው ተወላጅና ልዩ ጠባቂ የሆኑ አመራሮችን /ፍትሃነገስት በዛብህ የገንዘብ ጽ/ቤት ኃላፊንና አሁን የጥቃቅን ኃላፊ ሆኖ የተሾመውን አቶ ንብረት ታፈረን አጣሪ ኮሚቴ በሚል ሰይሞ ጉዳዩ ተድበስብሶ እንዲቀር አድርጎታል /ሙሉው መረጃ በአቶ ዮሐንስና በአቶ ፈንታሁን ሙጬ /ስልክ ቁጥር ... በተባሉ ሰዎች እጅ ይገኛል። ለክልሉ ፀረሙስና ኮሚሽንም አመልክተውና መረጃም አቅርበው እያለ ጉዳዩ በእነ አቶ ፋንታ ደጀን አማካኝነት አየታፈነ እንዲቀር ተደርጓል/
♦ አጠቃላይ ስራዎች ሽባ ሆነው እየቆሙ ናቸው ለአብነት ስንወስድ በትምህርት ዘርፍ ከተማ አስተዳደሩ ከሌሎች ዞኖች ጋር ሲወዳደር አፈፃፀሙ በጣም ዝቅተኛ ከመሆኑም ባሻገር እነደጀኔ የልማት ሰራዊት ተገንብቷል ብላችሁ የእውሽት ሪፖርት ስጡን እያሉ አስጨንቀው በመቀበል ከሚያስተላልፉት የእውሸት መረጃ ውጭ አንድም የተጨበጠ ስራ እየተሰራ አይደለም፣ ያው ለብሄር ብሄረሰቦች በዓል ተብሎ 69 ሚሊዮን ብር እየፈሰሰበት የተጀመረው የፅዳትና ውበት ስራም ቢሆን ለአንዲት ጠብታ ስራ በርካታ ገንዘብ እየፈሰሰበት ዛሬ ተሰርቶ ነገ የሚጠፋና ዘላቂነትና የህዝብ ባለቤትነት የሌለው ስራ ነው እየተሰራ ያለው
♦ በቅርቡ በተደረገው አመራር የማደራጀት ስራም ጎጠኛ በሆነ መንገድ የየራሳቸውን አካባቢ ተወላጅና ለዝርፊያና አፈና ተግባራቸው ተባባበሪ ይሆኑናል ያሏቸውን አባላት ያሰባሰበ አመራር ነው ያደራጁት። ግማሹ የፋንታ ደጀን፣ ግማሹ የስማቸው ግሩፕ ነው የተደራጀው፦ የአደረጃጀቱን ዝርዝር ስንመለከት
ሀ/ የአቶ ፋንታ ደጀን ቡድን /ደቡብ ጎንደር ተወላጆች/
1. ደጀኔ ሺባባው የብአዴን ጽ/ቤት ኃላፊ
2. ክብረት መሀመድ የገቢዎች ጽ/ቤ ኃላፊ
3. ፍቅር መኮንን የከተማ አገልግሎት የቴክኒክ ዘርፍ ምክትል ስራአስኪያጅ ከደብረታቦር በቀጥታ በልዩ ሁኔታ የመጣና የስራ ብቃት የሌለው
4. ክንድይሁን እገዘው የቤቶች ልማት ስራአስኪያጅ
5. መንግስቴ አምሳሉ የንግድና ትራንስፖርት ጽ/ቤ ኃላፊ
6. ሙላት ፀጋ የጥቃቅን ምክትል ኃላፊ ከብዙዎቹ ጥቂቶች ናቸው
ለ/ የአቶ ስማቸው ቡድን /ዘጌ ተወላጆችና የተለየ የጥቅም ትስስር ያላቸው/
1. ቢያድግልኝ አድምጠው የሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት ኃላፊ
2. ንብረት ታፈረ የጥቃቅን ጽ/ቤት ኃላፊ /የስማቸው ልዩ ምስጢረኛና ከቀበሌ በቀጥታ መጥቶ ሲቪል ሰርቪስ ትምህርት እንዲማር የተደረገና ትምህርቱን ጨርሶ እንደመጣ በቀጥታ የተሾመ/
3. ፍትሃነገስ በዛብህ የገንዘብ ጽ/ቤት ኃላፊ
4. ፋሲል ሙሉ የከተማ አገልግሎት የአገልግሎት አርፍ ምክትል ስራአስኪያጅና የከንቲባ ኮሚቴ አባል እንዲሆን የተደረገና የጥቅም ትስስር ያለውና የስራ ብቃት እንኳን የሌለው
5. ሙሉቀን አየሁ የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ
6. ነጋ ተመስገን የፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ
7. አላዩ መኮንን የከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ
4
8. ወርቅነህ ማሞ የጤና ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ
9. ሙሉጌታ ካሳ የትምህርት ጽቤት ምክትል ኃላፊ
10. ወ/ሮ አበባ ካህሊው የስማቸው የቅርብ ዘመድና ዘጌ ተወላጅ የ ከተማ ምክር ቤት ም/አፈጉባኤ ሆነው እንዲሾሙ የተደረጉት እውን በአጋጣሚ ወይንስ የሌላ አካባቢ ተወላጅና ከእነሱ ጋር የጥቅም ትስስር የሌለው ሰው የፖለቲካ እምነትና የስራ ብቃት ስለሌለው?! ለእነዚህ አመራሮች ከመኪና ምደባ ጀምሮ ምርጥ ምርጥ መኪና የተሰጣቸው እውን ለስራ ታስቦ ነው?!
11. ሌሎች የቀበሌ አመራሮችስ በአጋጣሚ ነው ከዘጌና ደቡብ ጎንደር ብቻ አየተፈለጉ የተሰገሰጉት?!
በአጠቃላይ የችግሩ መነሻ ስር ሰዶ የቆየው በአቶ ፋንታ ደጀንና በአቶ ስማቸው የጥቅም ትስስርና መርህን ያልተከተለ ጓደኝነት ምክንያት ነው። አቶ ፋንታ ደጀን-በመጀመሪያ የሊቦ ከምከም ወረዳ አስተዳዳሪ(ሊቀመንበር) እያለ አቶ ስማቸው ወንድማገኝን የአሁኑ ከንቲባችን ደግሞ የዚያ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ(ሊቀመንበር) ሆኖ እንዲመራ ከልማት ጣቢያ ሰራተኛነት ወደ ወረዳ ያስገባውና በኋላም አቶ ስማቸው ወንድማገኝ የደቡብ ጎንደር ዞን አቅም ግንባታ መምሪያ ኃላፊ በመሆን በተዋረድ አቶ ፈንታን ወደዞን ከሳበው በኋላ አቶ ፈንታ ደግሞ ወደ ክልሉ ብአዴን ጽ/ቤት ምክትል የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሆኖ ሲመጣ በመሳሳብ መርሃቸው መሰረት አቶ ስማቸውን በ2000 ዓ.ም የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት እና ብአዴን ጽ/ቤት ኃላፊ ሆኖ እንዲመጣ ያደረገው ባላቸው የቆየና ስር የሰደደ ትስስር ነው።
II. አቶ ፋንታና አቶ ስማቸው በከተማው ውስጥ የዝርፊያና የአፈና የአመራር ቡድን አደራጅተዋል።
♦ በዋነኛነት ከንቲባ ኮሚቴ በዋና ከንቲባው ልዩ ደጋፊዎችና ገለልተኛ ሊባሉ በሚችሉ ቡድኖች የተከፋፈለ ቢሆንም ገለልተኛ ተብየዎቹም ቢሆኑ ላለመዋጥ ወይንም ወንበራቸውን ላለማጣት የተቀመጡ ናቸው። አንዳንዶቹ የውስጥ አዋቂና ጠባቂ ተብለው የሚወሰዱ አድር ባዮች ናቸው።
♦ ከከተማው አመራር በስተጀርባ ሆነው የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርጉ፣ የዲፕሎማሲ ስራ የሚሰሩና የበላይ ጠባቂ /እንደራሴ/ ሆነው ቡድኑን የሚያጠናክሩ ነጋዴዎች፣ የክልል አመራሮች (እንደእነ ፋንታ ደጀን የመሳሰሉት)ና ስራቸውን የረሱ የሚመስሉ የፌዴራል ደኅንነቶች ነን ባዮችም አሉ።
♦ ከፌዴራል ደኅንነቶች መካከል /ለክትትል እንዲያመች/ አቶ ተሾመ በሚል ስም የሚታወቀውና በአሁኑ ሰዓት የእነ ከንቲባ ስማቸው ወንድማገኘውና የፋንታ ደጀን ቀኝ እጅ ሆኖ ከተለያዩ ባለሃብቶች ጋር ትስስር በመፍጠርና በተለያዩ ዘመዶቹ ስም ኮንዶሚኒየም ቤት ሳይቀር በእነ አቶ ስማቸውና በእነ አቶ ፋንታ ደጀን አመቻችነት እንደተሰጠው የሚነገርለትና እነዚህ አካላት በእሱ ስም አየተጠቀሙበት ያለ፣ ቀደም ሲል ግን ከአቶ ስማቸው ጋር ብዙም ጤናማ ያልሆነ ግንኙነት የነበረው/ የክልሉ ደህንንት ኃላፊን ለመጥቀስ እንወዳለን።
የከንቲባውን ጠባቂና አቀንቃኝ ቡድን አባላትን ስንመለከት፥
2. አላዩ መኮንን— በአሁኑ ሰዓት የከንቲባ ጽ/ቤት ሃላፊ
ከንቲባው ሲያገባ የሰርጉ የስር ሚዜ የነበረ፣ ልዩ ጓደኛው የሆነና የዚህ የዝርፊያና የአፈና ቡድን ዋና አስተባባሪ ነው።
አሿሿሙን ስንመለከት
♦ ከዚህ ቀደም የፎገራ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ የነበረና በኋላም በአቶ ስማቸው አቀነባባሪነት የባህር ዳር የከተማ ግብርና ኤክስቴንሽን የስራ ሂደት አስተባባሪ ሆኖ እንዲመጣ የተደረገ
5
♦ ከስራ ሂደት አስተባባሪነት በቀጥታ የህብረት ስራ ማህበራት ጽ/ቤት ሃላፊ ሆኖ የተሾመ
♦ በኋላም በኅብረት ስራ ጽ/ቤት ኃላፊነት ቆይታው ሁለት ወር ሳይሞላው የከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ ሆኖ በአጭር ጊዜ የተሾመ
በአሿሿሙ ዙሪያ የነበረው ችግር
♦ ያለበቂ ግምገማና የሌሎች የድርጅት አመራሮች እውቅና በከንቲባው ፍላጎትና የቅርብ ግንኙነት ብቻ መሾሙ
♦ ከአደረጃጀት መርህ በወጣ መንገድ በተግባር አፈፃፀሙ ሰይገመገምና በስራውም ሳይታይ ከኅብረት ስራ ማህበራት ጽ/ቤት ኃላፊነት ወደ ከንቲባ ጽ/ቤት ሃላፊነት በአጭር ጊዜ ውስጥ መሾሙ
♦ በየደረጃው ያለው ስራ አስፈፃሚ እንኳን በአግባቡ ሳያውቀው /በቂ ግንዛቤ ሳይይዝ/ በድብቅ እንዲሾም መደረጉ
♦ የነበረው የከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጋሻነው ዳውድ ያለምንም ግምገማና አስተያየት ወደ ሌላ ሴክተር እንዲዛወር መደረጉ
አሁን አየደረሰ ያለው አጠቃላይ ጉዳት
♦ ይህ አመራር ሌሎችን በማስተባበርና መርህን ባልተከተለ መንገድ ተገቢ ያልሆነ አደረጃጀት በመፍጠር በአመራሩ መካከል ልዩነት በመፍጠርና የተወሰነውን ግሩፕ /ቡድን/ ብቻ በመያዝ አለመተማመንና ልዩነት እንዲፈጠር እያደረገ ይገኛል፣
♦ ከፍተኛ የሆነ የመንግስት ገንዘብም ያለአግባብ በአበልና በግብዣ ስም እንዲወጣና እንዲመዘበር ያደርጋል፣ ለከንቲባው በደላላነት የጉቦ አመቻች ሆኖ ይሰራል፣ ከግለሰቦችም ጉቦ ይቀበላል
♦ የከንቲባውን ፍላጎት ብቻ የማስተናገድ፤ ከታች ልዩልዩ ኢንፎርማል አደረጃጀት በመፍጠር በአመራሩ ላይ ስለላ ማካሄድና ማን ምን ይላል በሚል መርህን ሳይከተሉ ተደራጅቶ ለማጥቃት መታገልና አመራሩ በራስ ተማምኖ እንዳይሰራና ተሸማቅቆ እንዲኖር ማድረግ።
♦ ያለካቢኔው ውሳኔ በርካታ የእንቨስትመንት ቦታዎች ልክ ካቢኔው እንደወሰነ ተደርጎ ግምገማ ሳይደረግበትና የጋራ ግንዛቤ ሳይያዝበት ከባለሃብቶቹ ጋር ግለሰቡ በደላላው አማካኝነት በጥቅም በመደራደር ወደ ክልል ይተላለፋል/ ቦታው እንዲሰጣቸው ያደርጋል፤
♦ በየጊዜው የሚቀርበውን የኢንቨስትመንት ቦታ ጥያቄ ለካቢኔው አቅርቦ ለማስወሰንና ለክልሉ ለማስተላለፍ ከእያንዳንዱ ሰው 10,000 /አስር ሺህ / ብር እየተቀበለ ነው ለከንቲባ ኮሚቴው የሚያቀበርውና የሚያስወስነው፣ ለዚህም የግል ደላላ አለው
♦ ለአብነነት፥
የሆምላንድ ሆቴል ማስፋፊያ 5000 ካ.ሜትር ስፋት
የጋሳ ሆቴል ባለቤት 5000 ካ.ሜትር ስፋት ተጨማሪ ሌላ ቦታ
የአዝዋ ሆቴል ባለቤት 5000 ካ.ሜትር ስፋት ተጨማሪ ሌላ ቦታ
አቶ አንሙት ክንዴ 5000 ካ.ሜትር ስፋት ቦታ
አቶ አበበ /ወረታ ኮንትራክተር/ 5000 ካ.ሜትር /ከአቶ አላዩ የከንቲባው ጽ/ቤት ሃላፊና ከአቶ መንግስቴ አምሳሉ የንግድ ጽ/ቤት ሃላፊ ጋር ባላቸው የቅርብ ግንኙነት ምክንያት የተሰጠ፤
6
እዚህ ላይ ለምን ቦታው ተሰጠ የሚል ተቃውሞ ለማንሳት ሳይሆን አሰጣጡ በአቶ አላዩና በከንቲባው የግል ጥቅም ግንኙነት ላይ ተመስርቶ የተሰጠ በመሆኑና እነዚህ ግለሰቦች ውስጥ አብዛኛዎቹ ከንቲባውን አይዞህ እያሉና ያለእሱ ሌላ ሰው ሊመራን አይችልም፤ ይህንን ሰው ማጣት የለብንም በሚል የሚቀሰቅሱለትም ጭምር በመሆናቸው ነው። ምሳሌ የሆም ላንድ ሆቴል ባለቤት፣ የባህርዳር ሆቴል ባለቤት፣እንዲሁም አቶ እያሱ አዳምጤና አቶ አበበ የተባሉት ዋነኛ ተጠቃሾች ናቸው/
♦ በየጊዜው አለአግባብ በሆነ መንገድ ምክንያት እየተፈለገ ለግብዣ አየተባለ በርካታ የመንግስት ገንዘብ ህገወጥ በሆነ መንገድ ይዘረፋል /ለያውም ያለ ህጋዊ ጨረታ በተደጋጋሚ ሌክ ሾር በተባለ አንድ ሆቴል ላይ/ የተወሰነው ቡድን እየተሰባሰበ ይጋበዛል/
♦ ይህ አመራር ያለውድድር ከንቲባው የነበረበትን የቀበሌ/የመንግስት/ ቤት ለቆ ወደ ቀበሌ 3 የኪቢአድ ቤት ተሰጥቶት ሲሄድ ሌላው አመራርም ሆነ ቤት ፈላጊው ሰው በተያዘው ወረፋ መሰረት ተወዳድሮ ቤት ሳይሰጠው አቶ አላዩ ግን በቀጥታና አድልዖ በተሞላበት ሁኔታ እንዲገባ ተደረጓል
♦ በየአመቱ ለከንቲባ ጽ/ቤት ከ3 ሚሊዮን ያላነሰ የስራ ማስኬጃ በጀት አየተመደበ ለዝርፊያ ይውላል፣ ለልማት በጀት ሲጠየቅ ግን ገቢ የለንም በሚል ልማቱ ሽባ ሲሆን ይታያል። በርካታ ት/ቤቶች የተጎሳቆሉ ሆነው እያለና በዙሪያ ቀበሌዎች የሚኖረው አርሶአደርም የመንገድና የመጠጥ ዉሃ ይሟላልኝ ጥያቄ በየጊዜው እያቀረበ ምንም ምላሽ ሳይሰጠው ባለበት ሁኔታ የመንግስት ባጀት ግን ምክንያት አየተፈለገለት በግብዣ ሰበብ ሲዘረፍ ይታያል።
♦ አጠቃላይ በየጊዜው የሚመደበውን በጀት ዝርዝርና የከንቲባውንና የወሮበላውን ቡድን በጀት አጠቃቀም መረጃዎችን በተመለከተ አቶ የቆየ ወርቅነህ የተባለውን የፋይናንስ ባለሙያ በማስረጃነት መጥቀስ ይቻላል ስልክ ቁጥር ...
3. አብይ ሃይሉ/ባህርዳር/ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሃላፊ
ለከንቲባው የግል የህዝብ ግንኙነትና አማካሪ ሆኖ ሁኔታዎችንየሚያመቻችና የተመደበበትን የመንግስት ስራ ትቶ የግለሰብ ቅጥረኛ ሆኖ የሚሰራና ከዚህ በፊት የሳለበቂ ችሎታና ብቃት ከቀበሌ አስተዳዳሪነት በቀጥታ ወደልዩ ዞኑ የህዝብ አደረጃጀትና ተሳትፎ ምክትል ሃላፊነት ተሹሞ የመጣና በዃላም ያለበቂችሎታ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳይ ጽ/ቤት ሃላፊ ሆኖ የተሾመ
በዚህም የአሁኑ ከንቲባ የቀድሞ የህዝብ ግንኙነት አማካሪና የድርጅት ጽ/ቤት ሃላፊ የነበረው አቶ ስማቸው ከአቶ ይትባረክ ጋር በወቅቱ የነበራቸውን አለመግባባት ተጠቅሞ ለአሁኑ ከንቲባ ልዩልዩ መረጃ በማቀበል ጥቃት እንዲፈፅም በቂ ድጋፍ በመስጠቱ ምክንያት ወዲያውኑ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳይ ጽ/ቤት ሃላፊ ሆኖ በእድገት የተሾመ፤
ይህ ግለሰብ አሁንም ቢሆን ቢሮው ቀጭ ብሎ ስራ የማይሰራና በጽ/ቤቱና በየቦታው እየዞረ ለከንቲባው መረጃ በማሰባሰብና ቡድኑን በማጠናከር ስራ የተጠመደ፣ መደበኛ ስራውን የማይሰራና በዚህ ድርጊቱ ሁልጊዜ በክቡር ከንቲባውና በጭፍሮቹ አጋዥነት በየግምገማው ከፍተኛ እየተባለ ደረጃ የሚሰጠው ግለሰብ ነው።
በተጨማሪም ከዚህ ቀደም መንግስቱ የተባለው የክልሉ ወጣቶች ማህበር ሊቀመንበር የነበረ ግለሰብ ጋር በነበራቸው የጠበቀ ግንኙነት 5000 ካ.ሜትር ስፋት ያለው ቦታ ያለአግባብ እንዲያገኝ ሁኔታዎችን ያመቻቸ ነበር።
4. መንግስቴ አምሳሉ /የደቡብ ጎንደር ተወላጅ/
7
የንግድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት ሃላፊ ከንቲባውን ከክልል አመራሮች /ቤተሰቦቹ ከሆኑት/ ጋር በማገናኘት ውለታ የሚሰራለት /በተለይም ከክቡር አቶ አያሌው ጎበዜ ጋር በጋብቻ ባላቸው ትስስር ምክንያት /የአቶ አያሌው ባለቤትና የአቶ መንግስቴ ባሌቤት የቅርብ ዘመዳሞች በመሆናቸው/
ከእነ አቶ ፋንታ ደጀን ጋር በአገር ልጅነትና ዝምድና አማካኝነትና ባለቤቱ የፋንታ ደጀን የአክስት ልጅና የአቶ አያሌው ጎበዜ ባለቤትም የቅርብ ዘመድ በመሆኗ አማላጅና አቀራራቢ ሆኖ በመስራት የከንቲባውን ጉድለትና ችግር እየሸፈነ ያለ ባለውለታው ነው።
ይህ አመራር ከደቡብ ጎንደር ተሹሞ ሲመጣ ባለቤቱም በቀጥታ ያለውድድርና ያለበቂ ችሎታ ከፀሃፊነት ወደ የንግድ ጽ/ቤት ኤክስፐርትነት ተመድባ ከደቡብ ጎንደር እንድትምጣ ነው የተደረገው።
5. ደጀኔ ሺባባው /የደቡብ ጎንደር ተወላጅ/
ቀደም ሲል የምእራብ ጎጃም ዞን ብአዴን ምክትል የነበረና ከዚያም የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የአስተዳደርና ፀጥታ መምሪያ ሃላፊ የነበረ፤
እንዲሁም የከተማው የቤቶች ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ሃላፊ ሆኖ ተሹሞ የነበረና በአሁኑ ሰዓት የህዝብ አደረጃጀትና ተሳትፎ አማካሪና እንዲሁም የድርጅት ጽ/ቤት ሃላፊ ሆኖ የተመደበ
በዋነኛነት ባላቸው የጥቅም ትስስር ማለትም ከንቲባውን ከሌሎች የክልል አመራሮች ጋር /አቶ ፋንታ ደጀን የአቶ አያሌው ጎበዜ ባለቤት ዘመድ ነው/ በማገናኘትና በማስተባበርም ጭምር የሚያገለግል።
የተጭበረበረና ህጋዊ ያልሆነ ዲግሪ ይዞ የሚገኝ /12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት 1.2 እያለው በተጭበረበረ ማስረጃ ከግል ኮሌጅ በማኔጅመንት ዲግሪ ተመርቄአለሁ በሚል ፎርጅድ ማስረጃ ያለው፣ ይህንንም ማሰረጃ ለማቅረብ የማይችልእንዲያቀርብም ተጠይቆ ፈቃደኛ ያልሆነ፣ ሁልጊዜ የእነአቶ ፋንታ ደጀንና የአቶ ስማቸውን ጥቅም ለማመቻቸት ሲባል ከቦታ ቦታ እየተዘዋወረ አለአግባብ የሚሾም
የተሳሳተ የትምህርት ማስረጃ ይዞ መገኘት ብቻ ሳይሆን ከዚህ ቀደም የአዴት ወረዳ አስተዳዳሪ ሆኖ ሲሰራ በተሳሳተ መንገድ ከጥቂት ነጋዴዎች ጋር በመመሳጠር ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ዋጋ ያለውን የባህር ዛፍ ደን መቶ ሺዎች ባልሞላ ዋጋ በሙስና ለመሸጥ ሲደራደር በህዝቡ ትግል ሊቀር የቻለና ይህም በክልልሉ አመራርም ሆነ በከተማው አመራር የሚታወቅ ሆኖ እያለ ዝም ተብሎ የታለፈ /ለተጨማሪ መረጃ ዘላለም ልየው የተባለና የክልል ገንዘብ ቢሮ ባልደረባ የሆነና ስልክ ቁጥር ... የሆነን ደውሎ ማረጋገጥ ይቻላል/
አሁንም ቢሆን ከተለያዩ የሙስና ድርጊቶች ያልወጣ /የቤቶች ልማት ኃላፊ ሆኖ በአሸዋ ግዥና በቁሳቁስ አቅርቦት ከኮንትራክተሮችና ደላሎች ጋር በመመሳጠር በፈፀመው ሙስና ዘመናዊ መኖሪያ ቤት በአጭር ጊዜ ተጠናቆ የተሰራለት
ግለሰቡ ምንም የስራ ብቃት ባይኖረውም እነአቶ ፋንታ ደጀን ላደራጁት የዝርፊያ መዋቅር መሪነትና በቀጣይም ለሚያስቡት ሀገወጥ የጥቅም ማስከበር ስራ አጋዥ የሚሆን የሰው ኃይል ለመሾምና የማይፈልጉትን ደግሞ አሽቀንጥሮ ለመጣል ሲባል ቁልፉን ቦታ እንዲይዝ የተደረገ አመራር ነው
6. ጋሻው ወርቅነህ /የአዴት አካባቢ ተወላጅ /
የህዝብ ግንኙነት አማካሪና የዚህ ዘራፊ ቡድን አባል ነገር ግን ትግል ከማድረግ ይልቅ በቡድኑ ተሸብቦ እራሱን ለማቆየት ሲባል ብቻ ሽፋን ሰጪ ሆኖ የሚኖር አደገኛ ቦዘኔ ።
8
ምንም የስራ ብቃትና ችሎታ የሌለውና በራስ የማይተማመንሪርት እንኳን ወረቀትና እስክርቢቶ አገናኝቶ ለመፃፍ የማይችል የተግባር ሳይሆን የመድረክ ሰው/ እንደ በቀቀን የተባለውን መልሶ በማስተጋባት የሰራ የሚመስለው
ከንቲባውን የሚገመግሙና የሚታገሉ ታጋዮችን በማሸማቀቅ ችግሩን የሚያበርድለት ተላላኪ ነው
7. ፋሲል ሙሉ /ባህርዳርና ከፊል ደቡብ ጎንደር/
የገንዘብና አካባቢ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ሃላፊ ሆኖ የሚሰራ በከንቲባው ልዩ ፍላጎት ለከንቲባው ልዩልዩ መረጃዎችን በማቀበልና አማካሪም ጭምር ሆኖ በመስራት የተሾመ አሁንም ልዩ የጥቅም ትስስር ያለው፣
ለአብነት ይህ ሰው የገንዘብ ጽ/ቤት ሃላፊ የነበረ ቢሆንም ሌክ ሾርና ሌሎች ቦታዎች ላይ ተደጋጋሚና ጥቂቱን የግሩፕ አባላት ብቻ የሚያሳትፍ ግብዣ በማድረግ ያለአግባብ የመንግስት ገንዘብ ሲመዘበር ተባባሪ በመሆን የሚያገለግል ነው።
በሌላ በኩል የቡድኑ አባላት ማለትም አላዩ፣ አብይ፣ መንግስቴና እራሱ ፋሲል አለአግባብና በጥቅም ትስስር ብቻ ሌላው አመራር ተወዳድሮና በጋራ ታይቶ ሳይሳተፍ የመንጃ ፈቃድ ለልማት በመጣው ገንዘብ ቴዲ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋም እንዲያወጡ ሁኔታዎችን ያመቻቸ፣ እንዲሁም የከተማው የውሃ አገልገሎት ቦርድ ሰብሳቢ ሆኖ ተገቢ ባልሆነ መንገድ የውሃ ገንዘብ እያባከነ ያለና ይህም በውሃ አገልግሎት ሰራተኞች በተደጋጋሚ የሚነሳ ጉዳይ ሆኖ እያለ ማንም ሃይ ባይ ያጣ መሆኑ የሚታወቅ ነው
የከተማው ውሃ አገልግሎት የቦርድ ሰብሳቢ በመሆን ከ2 ሚለዮን ብር በላይ እንዲመዘበር ያደረገና ጨረታዎች ያለአግባብ እንዲሰረዙና ከእነሱ ጋር የጥቅም ትስስር ያላችው ሰዎች ያለአግባብ ጨረታውን እንዲያሸንፉ በማድረግ የገጠር ቀበሌዎች የውሃ ቁፋሮ ስራዎች እንዲጓተቱና ስራው እንቆም ያደረገ እንዲሁም የውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ስራአስኪያጅ ያለተፈላጊ ችሎታና መመሪያ ዲፕሎማ ሆኖ እያለ ለጥቅም ማስከበር ሲባል አቶ ተሾመ የተባለውን እንዲሾም ያደረገ
የከተሞች ቀን በመቀሌ ከተማ ሲከበር ከፋይናንስ ህጉ ውጭ በቀን 400 ብር አበል በመክፈል ከፍተኛ ገንዘብ እንዲመዘበር ያደረገ/ ከ1.2 ሚሊዮን ብር ባለይ በዚህ አግባብ ተመዝብሯል
አሁንም በዚህ የጥቅም ትስስር ከገንዘብ ጽ/ቤት ሃላፊነት ወደ ከተማ አገልግሎት ምክትል ስራ አስኪያጅነት የከንቲባ ኮሚቴ አባል ሆኖ ያለአግባብ የደሞዝ ጭማሪ ተደርጎለት የተሾመ
የደጀኔ ሺባባው የእናቱ የቅርብ ዝምድና ያላቸውና በዚህም የተነሳ በመደጋገፍ የተሾመ
በአጠቃላይ የስራ ብቃት የሌለውና ግዥዎች በከፍተኛ ምዝበራ እንዲፈፀሙ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ምዝበራ ሲያካሄድ የነበረ ግለሰብ ነው
የገንዘብ ጽ/ቤቱ ኦዲት ቢደረግ ከዚህ በላይ ችግሮች ይታዩበታልና
I. የክቡር ከንቲባው የግል የስለላና መረጃ አሰባሳቢ ቡድን አባላት የሆኑት /በአቶ አላዩ የበላይ ጠባቂነት የሚመራው ቡድን/ ፤
2. በፍሬ ሰላም የልዩ ዞኑ የወጣቶች ሊግ ኃላፊ በጥቅም ትስስር ተልእኮ የተሰጠውና ያለትምህርት ዝግጅቱና ያለችሎታው እዚህ ቦታ የተቀመጠ /በአሁኑ ሰዓት ለሌላው አመራር አይቻልም አየተባለ በልዩ ሁኔታ ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የዲግሪ ፕሮግራም በኤክስቴንሽን እንዲማር ከነፋንታ ደጀን ጋር በመነጋገር የተፈቀደለት/
9
3. አሰፋ አድማሱ የልዩ ዞኑ የህዝብ ግንኙነት ምክትል ኃላፊ በጥቅም ትስስር /ምክንያቱም ያለብቃትና ያለበቂ መመዘኛ ከቀበሌ ጥቃቅን ወደ ልዩ ዞን በሹመት በመግባቱ ተጠቃሚና የከንቲባው ልዩ ጠባቂ የሆነ/
4. በሰላም ይመኑ የልዩ ዞኑ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊና የከንቲባው አካባቢ /ዘጌ/ ል ጅሆኖ የከንቲባው ልዩ መልዕክተኛና ጠባቂው
5. ምንይችል ካሳው የሰፈነ ሰላም ቀበሌ ምክትል አስተዳዳሪ/የዜጌ አካባቢ ተወላጅ/የሆነና በከንቲባው ልዩ ፍላጎት አሰተዳዳሪ የነበረውን ሰው ያለምንም ጥፋት ከቦታው በማንሳት እሱን ተክቶ እንዲሰራ የተደረገ
6. እያያ ንጋቱ የግሽ አባይ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ በጥቅም ግንኙነት የተሳሰሩና በተለይ ባለፈው ግምገማ የሙስና ችግር በተጨባጭ አለበት ተብሎ በአባሉና በአመራሩ ቢገመገምም እርምጃ እንኳን ለመውሰድ ያልተቻለው በዚህ ምክንያት ነው። የአቶ ስማቸው /ከንቲባው/ የቅርብ ዘመድ ልጅ ባለቤትና ቤተሰብ በመሆኑ
7. ቢያድግልኝ አድምጠው /ዘጌ ተወላጅ/ የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ልማት ማስፋፊያ ጽ/ ቤት ሃላፊ የነበረና አሁን በርካታ ሙስና ፈፅሞ እያለ ወደ ሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት ኃላፊነት የተዛወረና በከንቲባው ልዩ ድጋፍ ያለውድድር በሰመር/ክረምት/ የማስተርስ ዲግሪ የሚማር
8. ሃብታሙ የኔአባት በጥቃቅን ተደራጅቶ ሃብት የፈጠረ ነጋዴ በዋነኛነት የገንዘብ ድጋፍ በመስጠት ይህን ግሩፕ የሚያጠናክርና ባለሀብቱንም ጭምር የሚያስተባብር ተብሎ ውክልና የተሰጠው ቢሆንም ብዙም ለእነሱ ታማኝ ያልሆነ
9. አለሙ ገሰሰ የልዩ ዞኑ የአስተዳደርና ፀጥታ መምሪያ የመረጃ ክፍል ሰራተኛና ለከንቲባው ልዩልዩ መረጃዎችን አጠናክሮ እንዲያቀብል የተመደበና መረጃ ለመውሰድና ለማጥቃት ሲል ብቻ ለአቶ በረከት ስምዖን ልሰጠው ስለሆነ ሰለከንቲባውና ስለከተማ አመራሩ ችግር የሚገልፅ መረጃ አምጡ እያለ የሚያጭበረብርና በሰው የሚነግድ ለከንቲባው የመረጃ ሰብሰቢና ጠባቂው የሆነና ስራውን የረሳ የግል ጥቅም አሳዳጅና በስራውም የማይተማመን በመሆኑ
IV. የውስጥ ጠባቂ የሆኑና ያለብቃታቸው የተሾሙ የከንቲባው አካባቢው ተወላጅና ልዩ ተልዕኮና ትስስር ያላቸው አመራሮች
1. ፍትሃነገስት በዛብህ /ዘጌ ተወላጅ/ የገቢዎች ጽ/ቤት ሃላፊ የነበረና አሁን ለዝርፊያ እንዲመች ተብሎ የገንዘብ ጽ/ቤት ሃላፊ የሆነና በስራም ብቃት የሌለው
2. ነጋ ተመስገን /ዘጌ ተወላጅ/ የፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ ምንም ብቃት ሳይኖረው የተቀመጠና አንድም የህዝብና የመንግስት ጉዳዮችን ተከራክሮ መርታትም ሆነ ማስከበር ያልቻለ
3. ዘላለም መሰረት /ዘጌ ተወላጅ/ የንግድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ /ብቃትንና ችሎታን መሰረት ባላደረገ መንገድ ያለአግባብ የተሾመና /ከዚህ ቀደም የጥጥቃቅን ባለሙያ ሆኖ በፈፀመው ምዝበራ ከፍተኛ የሆነ ቅሬታ እየቀረበበት እያለ ጉዳዩ ተድበስብሶ እንዲቀር የተደረገለትና አሁንም የውስጥ አርበኛ ሆኖ የሚሰራ
4. ሙሉቀን አየሁ /ዘጌ ተወላጅ/ የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊና ገለልተኛ መስሎ የከንቲባውን ሁኔታ አየተከታተለ የሚያማክርና አሁን ያለውድድር ትምህርት በክረምት እንዲማር የተፈቀደለት
5. ጋሻነው ዳውድ /ባህርዳር/ ያለበቂ የትምህርት ዝግጅት በዲፕሎማ ደረጃ ልዩ ዞን ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ሆኖ የተመደበ ለመኖር ሲል ብቻ የሚኖርና መረጃ አቀባይና የትግል ወኔ የሌለው /በአሁኑ ሰዓት ለሌላው አመራር ሆኖ መማር አይቻልም አየተባለ ለእሱ ግን በልዩ ሁኔታ ይታይለት
10
በሚል ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የዲግሪ ፕሮግራም በኤክስቴንሽን እንዲማር ከነፋንታ ደጀን ጋር በመነጋገር የተፈቀደለት
6. ባዘዘው ገላው /የከተማ አገልግሎት የአስተዳደር ዘርፍ ምክትል ስራአስኪያጅ የነበረ/
የከንቲባው ልዩ አማካሪና የጥቅም ተጋሪ የሆነና ፀረሙስና ክስ ሲመሰረትበት ሲል ሆን ተብሎ ከምክትል ስራአስኪያጅነት መልቀቅያ እንዲሰጠው የተደረገ.
ይህ ሰው ለምለሚቱ ባህር ዳር ለሚባል ማህበር 24 አባላት ሁለት የገበያ ቦታ በመስጠት ለ8 ወራት ያህል እያንዳንዳቸው በወር ከ5000 እሰከ 6000 ብር እያከራዩ ሲጠቀሙ ዝም ብሎ ይመለከት የነበረና የጥቅሙ ተካፋይ የነበረ
አሁን ጉዳዩን የፀረ ሙስና ኮሚሽን መከታተል ሲጀምር የ12 ኮንቴይነሮች ቁልፍ ምንይችል የተባለ የሰፈነ ሰላም ቀበሌ አስተዳዳሪ ሰብስቦ እንዲያመጣና ቀደም ሲል እንደተሰበሰበ አድርጎ ለከተማ አገልግሎቱ ገቢ እንዲያደርግ ያደረገ ሰው ነው።
ክትትል ከተጀመረ በኋላ ይህንን ጉዳይ በጋራ ከከንቲባው ጋር በመሆን እነዚህን ባለኮንቴይነሮች ጠርቶ በመሰብሰብና በማወያየት ቁልፉን ቀደም ብለው እንዳስረከቡ አድርገው እንዲያስገቡና ከተጠያቂነት ነፃ ለማድረግ ነው ጥረት ያደረጉት።
የዚህ ተባባሪ ደግሞ በዋነኛነት ምንይችል ካሳው የተባለው የሰፈነ ሰላም ቀበሌ ምክትል አስተዳዳሪና የከንቲባው የአካባቢ ተወላጅ ነው።
V. በአደረጃጀቱ ወቅት በከተማው በስፋት ይታይ የነበረው ህገወጥ አደረጃጀትና እንቅስቃሴ
የመልሶ ማደራጀቱን መጀመር ተከትሎ በርካታና ህጋዊነት የሌላቸው እንቅስቃሴዎች በከተማ አመራራችን ይታያሉ። በዋነኝነት የከንቲባው ቡድን የሚመራው የህዝብ እንቅስቃሴ ነበር፤ ከንቲባው ከሌለ ሌላ ሰው ይህችን ከተማ አይመራትም በሚል የሚደረግ ሩጫና ይህንንም በባለቤትነት ይዘው የተንቀሳቀሱ ባለሃብቶችና ግለሰቦች አሉ።
♦ አቶ በዛብህ የባህርዳር ሆቴል ባለቤት
♦ አቶ መሉጌታ የሆም ላንድ ሆቴል ባለቤት
♦ አቶ እያሱ አደምጤ ኮንትራክተርና የግንባታ ቁሳቁስ /ቀይአፈር ወይንም ሬድ አሽ አፈር/ በነፃ እየተሰጠው የሚሰራና የከንቲባው ጉቦ አቀባባይ የሆነው
♦ መንግስቱ የተባለው የክልሉ የወጣቶች ሊቀመንበር የነበረ ግለሰብ እና ሌሎችንም በማስተባበር በየጊዜው በክልል ቢሮዎች በመሄድ የክልሉን አመራር የማነጋገርና ከእሱ ውጭ ከተማዋን ሊመራ የሚችል ሰው የለም በሚል አግባብ ለማሳመን ከንቲባውም ሰፊ የሆነ የህዝብ ድጋፍ ያለው በማስመሰልና ለስርዓቱ ሳይሆን ለግለሰብ የስልጣን እድሜ መራዘምና መደላደል በማሰብ በስፋት በመንቀሳቀስ ግለሰቡ በስልጣን እንዲቆይ የተደረገ ሲሆን፣
♦ ይህንን የምህንድስና ጥበብ አፍላቂውና መሪው ደግሞ አቶ ፋንታ ደጀን የክልሉ የህዝብ አደረጃጀት/ህዝብ ግንኙነት? አማካሪና የከተማችን አንጋፋው የዝርፊያና አድሎ መፈፀሚያ ቡድን የበላይ ጠባቂ የሆነው አመራር ነው ።
ይህን አደራዳሪ ኃይል ሲያስተባብሩ የነበሩት ደግሞ
1. በፍሬ ሰላም የልዩ ዞኑ የወጣቶች ሊግ ኃላፊ
11
2. አሰፋ አድማሱ የልዩ ዞኑ የህዝብ ግንኙነት ምክትል ኃላፊ
3. በሰላም ይመኑ የልዩ ዞኑ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ምክትል ኃላፊና የከንቲባው አካባቢ ልጅ/ዘጌ/
4. ምንይችል ካሳው የሰፈነ ሰላም ቀበሌ ምክትል አስተዳዳሪ /የዜጌ አካባቢ ተወላጅና በቀበሌ ደረጃ ነጋዴውንና እነ ስማቸውን በማገናኘትና በጥቅም በማሰተሳሰር ዋና ድልድይ ሆኖ የሚያገለግል/
5. እያያ ንጋቱ የግሽ አባይ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ
6. ቢያድግልኝ አድምጠው /ዘጌ ተወላጅ/
7. ሃብታሙ የኔአባት በጥቃቅን ተደራጅቶ ሃብት የፈጠረ ነጋዴ
8. አለሙ ገሰሰ የልዩ ዞኑ የአስተዳደርና ፀጥታ መምሪያ የመረጃ ክፍል ሰራተኛየሆነና ለከንቲባው ልዩልዩ መረጃዎችን አጠናክሮ እንዲያቀብል የተመደበ ነው። ስለሆነም ይህ አካሄድ ስርዓቱንም ሆነ ህዝቡን እየጎዳ ያለና የሰማዕታትንም ደም ከንቱ የሚያስቀር በመሆኑ ሃይ ሊባል የሚገባው ስለሆነ ብርቱ ክትትልና ትግል ማድረግና ቆሻሻውን የማስወገድ ስራ ሊሰራ ይገባል እንላለን። ለዚህ ደግሞ አታጋይ ከሌለ ማንም አደጋ ውስጥ ስለሆነ ትግል ማድረግና ማስተካከል በጣም ፈታኝ ይሆናልና የሚመለከታችሁ ጓዶች ይህንን ተከታትላችሁ መላ ልትሉን ይገባል።
ስለሆነም ይህንን መረጃ በአውሬዎቹ መሃል ሆነን ስናቀርብ አንዳችም መረጃ ለእናንተ ሳይደርስ በእጃቸው ከገባ አውሬዎቹ አርደውን ሊበሉን እንደሚችሉ ብናውቅም ፍትህ የጠፋበትንና ዝርፊያ የተበራከተበትን ከተማ ለህዝባችን ነፃነትና ጥቅም መከበር ሲሉ በተሰውት አእላፋት ጓዶቻችንና ከሁሉም በላይ በቅርብ ቀን ባጣነው ባለራዕይውና ቁርጠኛ ክቡር መሪያችን ስም ችግሩን በመፈተሽ ነፃ እንደምታወጡትና የህዝባችንንም ጩኸት እንደምትመልሱት ተስፋ በማድረግ ነው። ጥርጣሬያችን ግን ባለፈው ዓመት ያን ያህል ትግል ተደርጎና ህዝቡም ከልቡ አምኖ ተስፋ አድርጎ ፍትህ እየፈለገ በነበረበት ወቅት በእነአቶ ፋንታ ደጀንና ጥቂት ሌሎች ደጋፊዎች የበላይ ጠባቂነትና አደራጅነት ችግሩ ሳይፈታ ይልቁንም የከተማው አመራር አደረጃጀት በፋንታ ደጀን ደጋፊዎች፣ በአካባቢው ተወላጆችና የግል ጥቅሙ አስከባሪዎች እንደገና እንዲጠናከር ተደርጓል። በቀጣይ ስለእነፋንታ ደጀን ተንኮል፣ ህገወጥ አደረጃጀትና በአንዳንድ የክልል አመራሮች ሽፋን ሰጪነት በክልላችንና በከተማ አስተዳደራችን አየተፈጠረ ያለውን ችግር በተመለከተም ተጨማሪ መረጃዎችን ለማድረስ እንሞክራለን። ቸር እንሰንብት!
“ዘላለማዊ ክብር ለትግላችን ሰማዕታትና ለባለራዕዩው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን”
“አድሏዊ አሰራርና ሙስና በትግላችን ይወገዱ”
እነ “ ጊዜ ይፍታው ነን”!!! ከባህር ዳር
( ማስታወሻ፦ በደብዳቤው ላይ የተለያዩ ስልክ ቁጥሮች የተቀመጡ ቢሆንም ቆርጠን ያስቀረናቸው መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን። ኢሳት)
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ
Thanks a lot for your comments.