የመለስ ዜናዊ መርዶና ሰሜን ኮሪያዊው ዘዴ (North Korean Style Mourners in Ethiopia)
በሰሎሞን ተሰማ ጂ. (semnaworeq.blogspot.com)

ONLY THE MOB and the elite can be attracted by
the momentum of totalitarianism itself; the masses have to be won by propaganda
(Hannah Arendt, 1951:341)

በተመሳሳይ
ሁኔታም፣ Hannah Arendt በናዚ ሂትለርና በራሺያ ቦልሼቪኮች ጊዜ የነበረውን ሁናቴ እንደሚከተለው ለማስታወስ ሞክራለች፡፡
Science
in the instances of both business publicity and totalitarian propaganda is
obviously only a surrogate for power. The obsession of totalitarian movements
with "scientific" proofs ceases once they are in power. The Nazis
dismissed even those scholars who were willing to serve them, and the
Bolsheviks use the reputation of their scientists for entirely unscientific
purposes and force them into the role of charlatans (345.
ሳይንስ፣ በንግድ
ማስተዋወቅና በፍጹማዊው አገዛዝ የፕሮፓጋዳ ስራ ወቅት ትክክለኛው የስልጣን ምትክ ጥሩ ማስረጃ ነው፡፡ የፍጹማዊው አገዛዝ እንቅስቃሴ
ለሳይንሳዊነት ያለው ጭንቀት ሁሉ አንዴ ስልጣን ላይ ከተቆናጠጠ በኋላ ያከትማል፡፡ ናዚዎች ሊያገለግሏቸው ሳይቀር ወዶ-ገብ የነበሩትን
ልሂቃን ወግዱ ብሏቸዋል፤ ቦልሼቪኮችም ቢሆኑ “የድንቅ ሳይንቲስቶቻቸውን” በጎ ስምና ክብር፣ ኢሳይንሳዊ ለሆነ ግባቸው ሙሉ ለሙሉ
አዋሉት፡፡ ይባስ ብሎም የ“ሳይንቲስቶቻቸውን” ፍቱን ምክር ወደ ጠንቋዮች
ሚና/ዋዛ አዘቀጡት፡፡
ምን ጭማሪ ያስፈልገዋል? ሁሉም
ነገር በኛም አገር ላለፉት አርባ ዓመታት ተከስቷል፡፡ ፍጹማዊው አገዛዝ ምሁራኑን “ልማታዊ” የሚል ታርጋ ለጥፎባቸው፣ የጋማ
ከብት ካልሆናችሁ.... “ጤናችሁን ይስጣችሁ!” ብሏል፡፡ የንግግሮቹ/የዲስኩሮቹ ይዘትና ቅርጽ ሳይቀር የአገዛዙ ፕሮፓጋንዲስቶች
ቅጂ ካልሆነ እንደመደብ ጠላት መታየት አለ፡፡ ብዙዎቹም ልሂቃን፣
“አልጋው
ትኋን ሆነ መደቡም ቁንጫ፣
“ይኼን ጊዜ ነበር በተገኘ መውጫ፡፡” ብለው
መውጣት የቻሉት ወጥተው ቀሩ፡፡ ያልቻሉትም፣ አንድም ለሥርዓቱ አደሩ፣ ህሊናቸው ያወካቸው ደግሞ በዝምታ ውስጥ አደፈጡ፡፡ የመንዙማ
ዘያሪው እንዳለው፣ “አውራው ዝም ብሎ፣ ኩኩ አለ እንቁላሉ፤
ወንዱ ገረድ ሆኖ፣ ሴቱ ሆነዋል ባሉ!”
ይሄው ነው፡፡ “ብዘበነ
ግርምብጥ፣ ማይ ንአቅብዕ” ነው፡፡ (ዘመኑ የተገላቢጦሽ ሲሆን፣ ወሀ ሽቅብ ይፈሳል” ለማለት ነው - በትግሪኛ፡፡

የመለሰ (ለገሠ) ዜናዊን
መሞትና ሥርዓቱ ለምን ምሥጢር እንዳደረገው ሳስብ የመጣልኝ የፍፁማዊ አገዛዝ እስከምን ድረስ እንደሚሄድ ነበር፡፡ ከአምስት ሳምንታት
በኋላ መርዶውን በይፋ ስሰማ ብዙም አልደነቀኝ፡፡ ወደ ኋላ ተመልሼ አገዛዙ ለአምስት ሳምንታት ያህል ያደረገውን የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ
ማጤን ጀመርኩ፡፡ የሚከተሉትን ስድስት አንኳር ነጥቦች አገኘሁ፡፡
አንደኛ፣ ሀ) ከሐምሌ
አስር ጀምሮ ስርዓቱ 40-60 በመቶ በተባለው ቀቢጸ-ተስፋ የቤት እንሰራለን ቅስቀሳው ላይ ተጠምዶ ነበር፣ በስራና ከተማ ልማት
ሚንስትሩ በኩል (ለአራት ሳምንታት ያህል የፈጀ/የጠነዛ ወሬ ነበር)፡፡
ለ) የለነዶን
ኦሎምፒክ ጨዋታዎች ሽፋንና የኦሎምፒክ ዝባዝንኬ ወሬዎች ተጋነው ለአስራ አምስት ቀናት ያህል እንዲስተጋቡ ተደረገ፡፡
ሁለተኛ፣ የአዲስ አበባ
ከተማ ከንቲባና የክፍለ-ከተማዎቹ ተወካዮች ሰማኒያ አምስት ሺ (85,000) ጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚንየም) ስራችንን በይፋ
ጀመርን የሚል አደንቋሪ ልፈፋ ላይ ለአምስት ሳምንታት ያህል ነበሩ፡፡
ሦስተኛ፣ የሙስሊም ወንድሞቻችንን
የመጅሊስ ምርጫ ጥያቄም “በቀበሌ በኩል እንጂ በመስጂዶች በኩል አይደረግም፤ ፈጽሞ አይሞከርም” በሚል አሰልቺ የመንግስት መግለጫና
ዛቻ ለአምስት ሳምንታት ያህል አጀበውት ነበር፡፡
በአራተኛነትም፣ “የፍትህ
ጋዜጣ ህትመት አይሰራጭም፣ እንዲያውም መቃጠል አለበት” በሚል ሸፍጥ የብዙኃኑን አይንና ልብ ወደዚያ አታካች ክስተት ለሦስት ሳምንታት
ያህል ጎተቱት፡፡
አምስተኛም፣ ለንደን ላይ
የተያዘችው የሀሺሽ አዘዋዋሪዋን ዲፕሎማት ጉዳይ እንደልማዳቸው ለአንድ ሳምንት ያህል ርእሰ ጉዳይ አደረጉት፡፡ (ነገሩን በደንብ
ላጤነው፣ የአዜብ መስፍን ሮም የገባችበት እለትና ዲፕሎማቷ ለንደን ላይ የተያዘችበት ወቅት ይገጣጠማል፡፡ ልብ ያለው ልብ ይበለው!)
ስድስተኛ፤ የፓትሪያርኩን
ሞትና ስለፓትሪያርኩም “ብጹወ-ቅዱስነት” በመገናኛ ብዙኃናቸው አማካይነት አደንቋሪ ወሬ ለህዝቡ ለፈፉ፡፡ (“ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ!”
እያልን ሰማናቸው፡፡)
ሰባተኛ፣ በነሐሴ 13
ቀን 2004 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ላይ፣ በተለምዶ የልደታ መልሶ ግንባታ የተባለው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የማውጣት ደዋኪና የከተማውን
ህዝብ የቤት ችግር “ዓባይን በማንኪያ” እንደመቆንጠር ያለው፣ ርካሽ ቁማር ቢያንስ ለአምስት ቀናት ያህል ተለፈለፈ፡፡

****************************************
ከወራት በፊት በALJAZEERA
እና በBBC ላይ ወደተመለክትኩት የኪም ኢል ሱንግ ሞትና የሰሜን ኮሪያን ህዝብ “ሀዘን” (በትዕዛዝ ማዘን “አዘን” ከተባለ) ያየሁትን
አስታወሰኝ፡፡ ከሁሉም የማትረሣኝ፣ ያቺ ሙሉ ወታደራዊ ልብስ የለበሰችው ዜና አንባቢ ነች፡፡ ማንበብ አቅቷት ስትነፋረቅ አስታውሳለሁ፡፡
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥኑ ዜና አንባቢም ቢሆን እንባ አያፍስ እንጂ የጋዜጠኝነት ስነ-ምግባር የጎደለው ስሜት ነበር ያሳየው፡፡ ታዞ እንደነበር
አያጠራጥርም፡፡ ማለቴ ተጽፎ የተሠጠው በዚያ ቃና እንዲያነበው ነበር፡፡ እንደታዘዘውም አደረገው፡፡ የዚህ አይነቱን ጋዜጠኛ በ1993
ዓ.ም መለስ ዜናዊ ራሱ “አዝማሪ ጋዜጠኛ” ብሎ ነበር የገለፀው፡፡ የሰጡትን ግጥም ትርጉም ሳያጤን መልሶ የሚያሰማ “የገደል ማሚቶ”
ነው ለማለት ፈልጎ ነበር እንደዚያ ያለው፡፡
የሆነው ሆኖ፣ ቀኑን ሙሉ፣
አዝማሪዎቹም ሲያዘምሩ ዋሉና ማታ ከአራት ሰዓት በኋላ “የበሰው መጣ!” ምንም የአሪስቶክራሲ ጠባይና የመሪነት ባህሪ የሌላቸው ጎበዞች
ፊታቸውን ወደ ካሜራው አዙረው እኛ እንደምናደርገው ባታደርጉ ወየውላችሁ የሚል ቀጭን ትዕዛዛቸውን ከቦሌ ተርሚናል፣ እስከ አራት
ኪሎው ቤተ-መንግሥት ድረስ አስተላለፉ፡፡
የክልል ፕሬዝደንት ተብዬዎቹም
በማግስቱ በካሜራ ፊት የሰሩትን ድራማ ቁጭ ብለው ሌሎቹ የወረዳና የቀበሌ ነዋሪዎቻቸው ሲሰረት በቴሌቪዥን ሊመለከቱ ወደመጡበት ተመለሱ፡፡
የአማራው ክልል፣ የደቡቡ፣ የሶማሌው፣ የትግራዩ፣ የቤንሻንጉሉና የጋንቤላውም ክልል የቀበሌና የወረዳ ካድሬዎቹ ዳይሬክት በሚያደረጉት
መሰረት አልቃሽ አቁሞ፣ ሻማ ለኩሶ ነጠላውን አዘቅዝቆ ተወነ፡፡ ወታደሩ በየጦር ካምፑ፣ ፖሊሱም በየመምሪያው መሰለ-ተመሳሰለ፡፡
የሚንስትር መስሪያቤቱና የመንግሥታዊ ድርጅቶቹ ሰራተኞች እንደዚያው የማያስቅ ኩመካቸውን የአዞ እንባቸውን እያነቡ መሰሉ-ተመሳሰሉ፡፡
ኪም ኢል ሱንግ፣ እድሜ
ልኩን “ታላቁ መሪ!” “ለዓለም ሁሉ አስተዳዳሪነት የሚበቃ አርቆ አስተዋይ!” ሰሜን ኮሪያንና ህዝቧን ከዲያብሎስ ሳይቀር “ነፃ
ያወጣ መሲህ!” ተደርጎ ነበር የሚታየው፡፡ ከሊቅ እስከ ደቂቅ፣ ከሚሊሻ እስከ ጄነራል፣ ከድንጋይ ጠራቢ እስከ ኢንቨስተር፣ ከጉሊት
ቸርቻሪ እስከ አስመጪና ላኪ ድረስ በትዕዛዝ በልቅሶና በሃዘን ጹናሚ እንዲመቱ ነበር የተደረጉት፡፡ ማን ከማን ያንሳል፡፡
አቶ መለስ ዜናዊም በተመሳሳይ
ሁኔታ ልቅሶአቸው እንዲደምቅ ተደረገ፡፡ አርቲስት ነን ባዮች፣ አትሌቶቹም በሀይሌ ገብረ ሥላሴ ፊታውራሪነት፣ የሃይማኖት መሪዎቹም
ተራበተራ ተንዘፈዘፉ፡፡ በአማራ ቴሌቪዥን ብሮግራም ላይ ያየኋትን አንዲት ሻምበል ግን ከልቤ ታዝቤያታለሁ፡፡ ፈር የለቀቀች አስመሳይ
ናት፡፡ እንኳን እሷንና አቶ መለስ ጄኔራሎቹንና ሌሎች ሹሞቹንም ቢሆን ያን ያህል አላንሰቀሰቀም፡፡
የኪም ኢል ሱንግን ስልጣን
ልጁ በ22 ዓመቱ እንዲወርስ ተደረገ፡፡ የአቶ መለስንም ስልጣን ልጃቸው እንድትወርስ ዳርዳርታ ሳይኖር ይቀራል? ከሆነም የፍፁማዊ
አገዛዝ መገለጫ ነውና እንዳይገርማችሁ፡፡ እኔ ግን ቀዳዊቷ እመቤት ያንን የመሰለ ግቢና ቪላ ላቃ መውጣትም ስለማትሻ ቀጣይዋ ቀዳማይ
ሚኒስትር እንደምትሆን ጠርጥረያለሁ፡፡ EFORTን ለማን ሰጥታ?!......
ጉዳዩን የዛሬ ሃምሳ አምስት
ዓመት ገደማ ወደኋላ ተመልሼ ላጤነው እገደዳለሁ፡፡ በ1949 ዓ.ም. የንጉሠ ነገሥቱ ተወዳጅ ልጅ ልዑል መኮንን ኃይለ ሥላሴ የሞተ
ጊዜ፣ በየክፍለ ሀገሩ የህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሾች አልቅሱ እየተባሉ በእንደራሴዎቹ ትዕዛዝ የሚያለቅሱ ነዋሪዎች ነበሩ፡፡ ከአልቃሶቹ
አንዷ አንጀቷ ያረረ ታዲያ እንዲህ ብላ ገጠመች፤
“የልዑል
ጌታዬ እናት ከሴቶች በለጠች፤
ልዑል መኮንንን ሁለት
ጊዜ አማጠች፡፡”
የሚገርመው፣ የወላይታ
ሶዶው-፣ የእደርታው፣ የኤርትራው፣ የጋንቤላው፣ የሶማሌው፣ የአሳይታው፣ የሀረርጌውና የጎፋው ሁሉም ማልቀሱና መገደዱ ሳያንስ ለልዑል
መኮንን ሆስፒታል (የዛሬው ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ነው) ማሰሪያ ተብሎ እስከ 1957 ዓ.ም ድረስ ገንዘብ እንዲያዋጣ ይገደድ ነበር፡፡
ዛሬም ቢሆን የህዝቡን በቀደዱለት ቦይ መፍሰስ የሚመለከቱ ጮሌ ካድሬዎች “የቀዳማይ ሚንስትር መለስ ዜናዊን ሕዳሴ ግድብ ማስፈጸሚያ”
እያሉ የሕዝቡን ጥሪት ከአፉ ላይ እንደሚነጥቁት ጥርጥር የለኝም፡፡ (ታሪካችን ሁሉ “ቀኝ ኋላ ዙር!” ነው፡፡) ምንም አዲስ ነገር
አይደለም፡፡
በየካቲት 8 ቀን
1954 ዓ.ም የእቴጌ መነን መሞት ተከትሎም በዘመኑ አንድም ያልተሰራ ድራማ አልነበረም፡፡ በጣም በተለየ አኳሁን ነበር ህዝቡ እንዲያለቅስና
እንዲያዝን የተደረገው፡፡ በኢትዮጵያ ምድር ሕዝብ በትዕዛዝ ወይም በአዋጅ ሲያዝን ምናልባትም ብዙ ጊዜ ሊሆን ይችላል፡፡ በዘመናችን
ግን ስናይ በዚህ በወያኔ ጊዜ ምናልባትም ለሦስተኛ ጊዜ ነው፡፡ በ1989 ዓ.ም የኃየሎም አርዓያ ሞት የተካበደ ነበር፡፡ የጥላሁን
ገሠሠ የ2001 ዓ.ም ቀብር ጉዳይም በትዕዛዝ የተከናወነ ቲያትር ነበር፡፡ (ቲያትሩን አሳዛኝ የሚያደርገው፣ ጥላሁን ገሠሠ ሞተ
በተባለ ማግስት የሡዳኑ ሰው-በላ ዑመር አልበሺር ጉብኝት ጋር መያያዙ ነው፡፡ እንደሚታወቀው፣ የዓለም ዓቀፉ ፍርድ ቤት በዳርፉርና
በሌሎችም የሱዳን ግዛቶች በፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል “Genocide Watch” ለፍርድ ሊያቀርበው ይፈልገዋል፡፡ የወያኔ መንግስትም
የጥላሁንን ሞትና ሥርዓተ-ቀብር የዓለም ዓቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት ለማሳት ተጠቅሞበታል፡፡ ከዚያ ቀጥሎ በ2004 ዓ.ም በመስከረም
10 ቀን፣ በዚያ ሞገደኛ አሞራ ሰበብ ገደል ገብተው የሞቱት የወያኔ ሙዚቀኞች የቀብር ስነ-ሥርዓትም ከፍ ያለ ነበረ፡፡

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ
Thanks a lot for your comments.